Thursday, November 12, 2015

Thanks Giving



   Whereas the duty of all nations to acknowledge the providence of Almighty God, to obey his will, to be grateful for His benefits ,and humbly implore His protection ,aid and favors…
Now therefore ,I do recommend and assign the 26th of November next, to be devoted by the people of these  states to the service of that Great and Glorious Being.Who is the beneficent Author of all the good that was ,that is ,or that will be that we may then all united in rendering unto Him our sincere and humble thanks for His kind care and protection of the people of this country , and for all the great and various favors which He has been pleased of confer upon us.
Our founding fathers openly recognized God. They were aware of our need for God if we were to be a healthy nation .George Washington said: ‘’ It is impossible to rightly govern the world without God and the Bible.’’ They know that if the nation was going to work its people needed to voluntarily live by God’s rules.
Times have changed .We may be the only culture in the world that openly acknowledges God in our constitution,on our money , and on Thanks giving, but refused to allow God to be named in any of our public institutions. As a nation we are working hard to push God out of our lives.
Ignoring God isn’t unusual.The history of the world is a story of people turning away from God.Amazing,God hasn’t turned away from us yet.But if we do not repent,He will.
Government can not turn us back to God. Turn back to God requires a change of heart.When get out hearts fixed,our priorities lineup, and things work better.
You can get this change of hearts by giving up your old life and turning to God. He sent His Son Jesus to close this huge gulf between us and God.So when we turn to God in the name of Jesus, we are acceptable as if we never sinned-the Bible calls it being clothed with Jesus’ clothes in front of God. In the name of Jesus you can belong to God and busy yourself in His world. In the name of Jesus you can once again belong to others. When you belong to others, your life won’t be sucked dry –you’ll be like a mountain spring fuller and fresher than you ever imagined.That’s because you keep turning God to fill you up,and He has all the resources in the universe at His command. It’s like being wealthier than you could ever imagine.
So I hope you will turn your face towards God this Thanks giving.Do more than Thank Him for good thanks giving will become a year-round event in your life.
‘’ Blessed is the nation whose God is the Lord: Behold the eye of the Lord is upon them that fear Him, upon them hope in His mercy’’ , Psalm 33: 12,18.
‘’Righteousness exalts a nation, but sin is a disgrace to any people.’’Proverb 14:34.
‘’ For God so loved the world that He gave His only begotten Son that whosoever believeth in Him should not perish, but have everlasting life.’’ John 3:16.
‘’ He that believeth on the Son hath everlasting life: and he that believeth not the Son shall not see life: but the wrath of God abideth on him’’ John 3:36.
‘’ Whosoever shall call upon the name of the Lord shall be saved .’’ Romans 10:13
              Thanks Giving Prayer
Dear God :Thank you for the wonderful gifts you have poured out on our nation.In the name of Jesus,who died for my sins,forgive me and forgive our nation for enjoying your gifts while trying to live without you. I repent of how I have been living and gratefully give my heart to you today. Help others in our nation to turn to you .Amen!
                              Source: from Tract League blog

If you want to read more click here: http://tehadesothought.blogspot.com

Sunday, October 4, 2015

ሚስጥረ ቁርባን

''ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንስቶ ባርኮ ቆርሶም ሰጣቸውና እንካችሁ ይህ ስጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንስቶ አመስግኖ ሰጣቸው ሁሉም ከእርሱ ጠጡ፡፡ እርሱም ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፡፡ '' ማርቆስ 14:22-23

  በተለያየ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ህይወት ያገኛል፡፡ ስለሚል ቁርባን ያጸድቃልን ?
  • ቅዱስ ቁርባን በቅዳሴ ጊዜ ወደ እውነተኛ የክርስቶስ ደምና ስጋነት ይቀየራልን ?
  •  ስጋውና ደሙን መውሰድ ያለበት ማን ነው? የሚሉትና የመሳሰሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳስሳለን፡፡
   በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከተደነገጉት 7 ዓይነት ሚስጥራት መካከል አንደኛው ሚስጥረ ቁርባን በመባል ይታወቃል፡፡ ቅዱስ ቁርባን  ወይም የጌታ እራት ብለን የምንጠራው ስርዓት የተደነገገው በጌታ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ ከወጡበት ዕለት ጀምሮ እንዲፈጽሙት በእግዚአብሔር የታዘዙ በመሆኑ እስከዛሬ ድረስ ይጠብቁታል፡፡ ነገር ግን ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ጥላ በመሆኑ ና ክርስቶስ የገዛ ደሙን አፍስሶ ከሐጢያታችን አጥቦ ከዓለም ስላወጣን አርነታችን እውነተኛ ፋሲካ ክርስቶስ ሆኖልናል፡፡ ስለዚህም በጌታ እራት ጊዜ በድምቀት የምናስታውሰው ትልቁ ነገር የጌታ ሞትና ትንሳኤ ነው፡፡ የፋሲካ እውነተኛ ትርጉሙም ስለ ሐጢያታችን የሞተው የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ ነው፡፡

  ከጊዜ ወዲህ ግን ስለ ጌታ እራት ወይም ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚሰጡ ትርጉሞች እንደየ ቤተ እምነቱ ሁኔታ መለያየትን አምጥቶአል፡፡ ለመሆኑ የጌታን እራት በመውሰድ ይጸደቃልን ? ይህ ዋነኛ ጥያቄ በቅድሚያ መመለስ አለበት፡፡ ብዙዎች የጌታን እራት በመውሰዳቸው ምክንያት እንደሚጸድቁ ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ጽድቅን ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን እውነት ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ፅድቅ እንዴት ይገኛል? ብለን በሌላ ትምህርት ላይ አንስተን እንደነበረ ልብ በሉ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን ጽድቅ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ነው፡፡ ዮሐ.3፤16፣ ሮሜ.6፤20፣ ሮሜ 10፤9፡፡ ታዲያ '' በስጋዎ ደሙ ይጸደቃል'' የሚለው ትምህርት ከየት የመጣ ነው ? ካልን በዮሐንስ ወንጌል 6 ላይ ከተጠቀሰው ቃል መነሻ ተደርጎ እንደመጣ የሚታመን ሲሆን ቃሉም '' ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው አለ፡፡'' ቁ.54 ይላል፡፡

   ክፍሉን በጥንቃቄ ብናጠና ከመጀመሪያው ጀምሮ ስለ ምን እንደሚያወራ መመልከት ይቻላል፡፡ ከቁ.1-14  ብዙ ሰዎች ፡ማለትም ሴቶችና ህጻናትን ሳይጨምር ወንዶች ብቻ 5 ሺህ  ሆነው ወደ ጌታ የመጡበት ፣ከዚያም 2 ዓሳ ና 5 የገብስ እንጀራን ባርኮ ሁሉም እንደሚፈልገው ወስዶ ጠግቦ 12 ቅርጫት ቁርስራሽ የተነሳበት ታሪክ እናነባለን፡፡ ከዚያ ቁ. 15 ላይ ህዝቡ ኢየሱስን በድንገት ነጥቀው  ለማንገስ ሐሳብ እንዳላቸው አውቆ ከእነርሱ ፈቀቅ እንዳለ ያስረዳል፡፡ ከቁ.16 እስከ 25 ድረስ ህዝቡ በተለያየ ቦታ ፈልገው ፈልገው ፡በሁዋላ ላይ ግን እንዳገኙትና አንድ ጥያቄ እንደጠየቁት ተጽፉዋል፡፡ '' መምህር ሆይ ወደዚህ መቼ መጣህ? አሉት፡፡ ኢየሱስም መልሶ እውነት አውነት እላችሁዋለሁ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለበላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም፡፡ለሚጠፋ መብል አትስሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ህይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ስሩ፡፡እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና፡፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ስራ እንድንሰራ ምን እናድርግ አሉት'' ኢየሱስም መልሶ ይህ የእግዚአብሔር ስራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው፡፡'' ቁ.27-29፡፡ ቁልፍ ነገሩ እዚህ ጋር ነው ያለው ፡፡ ምዕራፉ የሚተነትነው ስለሚበላ የስጋ ምግብ ሳይሆን በክርስቶስ ስለማመን ነው ፡፡ ከዚያ በሁዋላ ያሉትን ጠቅላላ ቁጥሮች ብንመለከት ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱን በማመን ስለሚገኝ የዘላለም ህይወት እርሱም የህይወት እንጀራ በመሆኑ '' የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም፡፡'' ቁ.35

  በእርግጥ ስጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ በሚለው ትምህርቱ ደቀ መዛሙርቶቹ እንኩዋ ሰምተው እንደተሰናከሉ እናነባለን ፡፡ የጌታ መልስ ግን '' ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው እንጂ ስጋ ምንም አይጠቅምም ፤እኔ የነገርኩአችሁ ቃል መንፈስ ነው ህይወትም ነው፡፡'' ቁ.63፡፡ ስለዚህ ቃሉ በአጠቃላይ ስጋዎ ደሙን ወይም የጌታ እራት የሚባለውን ስርዓት ለማስረዳትና ትዕዛዝ ለመስጠት የተጻፈ አይደለም፡፡ እርሱን የተነናገረበት ሌሎች ክፍሎች አሉ፡፡ ክፍሎቹ በሙሉ የሚያስረዱት የጌታ እራትን በመውሰድ ስለሚገኝ ጽድቅ ሳይሆን ፡ ድነት ያገኘንበትን ሞቱን እንድናስብ ነው፡፡ ለነገሩ ከስቅለቱና ከሞቱ በፊት የጌታን እራት በመውሰድ እንድንጸድቅ አስቦ ቢሆን፡ ለምን ያን ሁሉ ዋጋ ይከፍላል?፡፡ የመስቀል ላይ ጣሩ፣ የደሙ መፍሰስና ሞቱ በእርሱ አምነን እንድንድን የግድ አስፈላጊ ና ለሐጢያታችን ክፍያ መሆን ስለነበረበት የተደረገ ነው፡፡ ስለ ጽድቅም እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር አልተጻፈም፡፡ የጽድቅ መንገድ እርሱ እንዳለው '' እኔ መንገድ፣ እውነትና ህይወት ነኝ፡ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም '' ዮሐ.14፤6 ፡፡ ብሎአል፡፡ የጽድቅ ብቸኛ መንገድ ክርስቶስ ነው፡፡

    የጌታ እራት ትክክለኛ ትርጉም ምንድን ነው?
  • የጌታን ሞትና ትንሳኤ መናገሪያ/ማወጂያ/
  •  የቅዱሳን ህብረት ማድረጊያ፡፡ ይህም በአንድነት በምንወስደው ማዕድ በክርስቶስ የተሰጠንን ክርስቲያናዊ ህብረት የበለጠ እናጠናክራለን፤እርስ በርስም እንተናነጻለን፡፡/1ቆሮ.10፡16-18
  •  የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ህብረት ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ከቅዱሳን የእርስ በርስ ግንኙነት በተጨማሪ ከጌታችንም ጋር ህብረት እናደርጋለን፡፡ ቁ.21
የጌታን እራት ማን ሊወስድ ይገባል?
  • የጌታን እራት በክርስቶስ ያመኑ አማኞች ሁሉ ሊወስዱት ይችላሉ፡፡
  •  አንዳንድ ቦታ እንደየ አካባቢውና ህብረተሰቡ ተጨባጭ ሁኔታ ቤተክርስቲያን በአወሳሰድ ጉዳይ የራሱዋን ድንጋጌ ልታወጣ ትችላለች፡፡ ይህም ስርዓቱ መንፈሳዊ ትርጉሙን እንዳያጣ እና እንደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ሁኔታ እንዳይፈጠር በማሰብ ነው፡፡ 1ቆሮ.11፤17-31
  •  በሐጢያት ለመቀጠል ያልወሰነ አማኝ ሁሉ ራሱን መርምሮ መውሰድ ይችላል፡፡
   በእርግጥ ብዙ ጊዜ  ከጌታ ይልቅ፡ ለጌታ እራት የመጠንቀቅ ልማድ ብዙ ምዕመናን ላይ ይስተዋላል፡፡ ይህ ማለት ልባችን ውስጥ ያለውን ክርስቶስን በመፍራት ንስሐ ልንገባ፣ የበደሉንን ሰዎች ይቅር ልንል ወይም ይቅርታ ልንሰጥ ይገባል እንጂ የጌታ እራት በመጣ ቁጥር ብቻ የምንቀደስና የምንሩዋሩዋጥ ከሆነ፡ ድንገት የሚሆነው ምጻቱ ጊዜ ምን ሊውጠን ነው? ከዚህ በተጨማሪ ድል እና ድነትን ያገኘንበትን የሞቱን መታሰቢያ፡ የሙታን ተስካር እንደሚዘከር ያለ ስርዓት ማካሔድም ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሞቱ ነው ሰይጣን ድል የተደረገው ፣ ሞትና መውጊያው የተሸነፉት፡፡ ሞቱ  ፣ የደረሰበት መከራና እንግልት ሁሉ ቢያሳዝነንም ግን ደግሞ በትንሳኤ የተነሳ ጌታ ነው፡፡ በዕለቱ  የንስሐ መንፈስ ያስፈልጋል ፡ደግሞ ደስ ሊለንና ልንዘምርም ይገባል፡፡

ትርጉሙ ሳይገባን መውሰድ የሚያስከትለው ቅጣት:-
  •  ሳይገባው የጌታን እራት የሚወስድ የጌታ ስጋና ደም ባለ ዕዳ ይሆናል፡፡1ቆሮ.11:27
  • ፍርን ያመጣል፡፡ ቁ.29
  •  ቆሮንቶሶች በጊዜው እንደ ደረሰባቸው አይነት ህመምና ሞት ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ 1ቆሮ.11፡30
ስለሆነም ወደ ከበረው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራት ከመቅረብዎ በፊት ሁለት ወሳኝ ነገሮን መወሰንዎን አይዘንጉ ፡-

1-እውነተኛ ንስሐ መግባትዎትን

2-ስለ ዓለም ሁሉ ተሰቅሎ የሞተውን ደግሞ በሶስተኛው ቀን የተነሳውን መድኀኒዓለም ክርስቶስን ማመንዎትን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ይህ ሲሆን አይደለም ለጌታ እራት ፡ለመንግሰተ ሰማይም እንኩዋ አይሰጉም፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በነገር ሁሉ ያግዘን ፡፡ አሜን!


Saturday, September 5, 2015

Gospel Report



Gospel Outreach Activity Report

I started writing successive spiritual articles since 2014 under the theme Tehadeso thought blog /Reformation thought/. Below I am going to present a report on the deeds attained with the will and help of God.
First of all, I thank my God for putting this love for the primeval Ethiopian orthodox church and the people under it. I thank those who have been of assistance to me in their prayers as well as material support and I say God Bless you all.
Salvation is the main focus of this blog and at times salvation related reformation messages are posted. Some of the articles posted in the area of salvation, include: mystery of salvation, pressing memorandum, dispatch from hell, and did you repent? There are also articles released on Face Book to disseminate the message of the gospel with acumen. Some of the topics include: for Visa seekers, Free Scholarship opportunity, job vacancy, news Book, and wedding invitation.
Salvation related articles are also posted relating to Christian holidays. Topics include: Easter, Christmas messages, about the resurrection, the passion week of Christ and currently preparations have already been made to post articles on upcoming holidays such as thanks giving and the New Year. Many Ethiopians are strewn all over the world and chances are most of them observe two holidays (using the western calendar as well as the Ethiopian calendar).  Most of the articles are suited to serve this very purpose. Some are born overseas and they don’t speak the local language and hence attempts are made to reach the group in English. Articles such as urgent message, don’t delay, and Mystery of salvation are among them. Plans to translate these articles in to oromigna and Spanish languages are completed. America is home for many immigrants from different parts of the world and a concerted effort will be made to reach these people in their respective native languages in the future. 
Moreover, articles are posted for those who are already saved to encourage them in their spiritual life. Some of the posts in this regard include: before getting too late, you shall never wash my feet, the minister and his service, giving and taking away, reign, God’s thought, and the four moons in relation to the end of the age. Some efforts are also being made to educate and edify the Ethiopian Orthodox Church followers and encouraging results are attained. Issues covered in this area of ritual observances include: there are how many types of bible?, the apocrypha books, intercession, the role of holy angels, Zeker /commemoration of holy Angels and Martyrs/,  and  Yemut Teskar /memorial for the  dead/,  and authority of the priest, etc…
Preparations to post successive articles on Dogma and canon, the mystery of communion, and fasting are completed. Until now, gospel messages as well as related teachings are disseminated using face book, email, Google plus, phone, text, and viber.  Face book users data indicate that thousands have benefited from these posts. People in   24 countries around the world viewed these articles and the countries are stated below: USA, Ethiopia, Canada, England, Kuwait, Bahrain, the Netherlands, Sudan, France, Poland, Ukraine, Egypt, Germany, Switzerland, South Africa, Indonesia, Burundi, Yemen, Italy Eritrea, Norway, Hungary, Kenya, Romania and Saudi Arabia.  Your extended effort in receiving and disseminating these messages into the different parts of the world will not go without being appreciated and God bless you all for that!
The gospel of Matthew chapter 28 verses 18 through 20 instructs us to “go into the entire world….” and this blog is part of that great commission. Among the 7 billion world population, around 2 billion people use the internet so it is a good method to disseminating the Gospel. No one knows with absolute certainty how many of these users are saved. However, unless we make a valiant effort to use these methods, others would come and baptize these people with their own ideologies. (Please refer to the appendix at the end of this report to view the potential gospel preachers can have via the internet).
Under this ministry, there are 12 Face book groups with diverse interest and focus. The following table shows the 12 groups with their number of attendees and their focused interest.


Group #
Number
of attendants
Focus(interest)



1
3792
Focuses in the area of Christian songs and poems
2
40
Ethiopian college students in the USA
3
326             
Live in the Arab world and meet to pray and exchange topics
4
2311
People with passion and vision for Ethiopia
5
1583
Focuses on the move of the Holy Spirit in Ethiopia
6
20
Appear to be ‘non-believers’ and their main focus is Ethiopian politics
7
7657
Focuses on the gospel
8
149
Members of an Ethiopian based church with the main focus of edifying each other
9
New
Spiritual vision for women around the world
10
475
The ‘Jesus Saves’ Group
11
New
Orthodox Tewahedo and Geze related salvation messages
12
New
Reformation Bible School and  focuses  on deeper spiritual  teachings





In Addition, there are 9326 viewers on Google plus and 29 followers. At least one article in regards to salvation is posted on Google plus at least once a week both in English and in Amharic.  51 different messages have been released on the Reformation thought blog and were viewed by over 13068 people. The biggest volume of viewers are from the USA (10,060) followed by Ethiopia (1129).
Furthermore, the blog presented some video messages and teachings by priests who believed in Jesus Christ and initially were ministers in the Ethiopian Orthodox Church. When needed, some article excerpts were presented from different ministers and this will continue frequently.
Most of these messages are delivered using texting on mobile phones. Currently, I hold more that 360 addresses and recipients in my cell phone. 268 people receive messages using Viber. Among these, over 60 of them are in groups that contain 19 to 25 members. Many of these group members are trusted in sharing these messages to family members and relatives. May the Lord bless your efforts and deliver your families and relatives. There are also lots of email users. I have received complaints from users who wish to receive our messages through email rather than on their cell phones due to the fact that they were not able to view documents written in Amharic. 
For those without access to any of these technologies, normal postal mailing system has been set up. This service deals with sending salvation messages using physical address.  Some have sent these mails to their families, friends and bosses and played their part.  May God bless all of you!
By God’s grace, we came this far. Until the whole world is saved or until the return of our Lord and Savior Jesus Christ, we will use whatever means to disseminate and preach the gospel. We will strengthen and build on these platforms.  In the near future, we plan all Christians to witness the gospel to at least ten people for witnessing purposes. We also plan to share our idea with those who have love for souls and ask them to intercede to these souls at their homes. We believe witnessing the gospel cannot be left for ministers alone and our plan is to make all Christians to be witness of the gospel.
There are also grand plans that are not listed in this report. We got to pray for the Lord to help us in all our efforts to stand together for the gospel. 
The God of heaven will make us prosper, and we his servants will arise and build.Amen!

Your Servant in the Lord,
Beneyam Befikadu Aboye
Silver Spring
Maryland

ረፖርት



                             በወንጌል ስለተሰራው ስራ የቀረበ ሪፖርት
ተሐድሶ ቶውት በሚል በተከታታይ መንፈሳዊ ጽሁፎችን ማቅረብ የተጀመረው በ 2014 እ.አ.አ. ሲሆን በዚህ ብሎግ እስካሁን በእግዚአብሔር ፍቃድ የተሰሩትን ክንውኖች ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ በቅድሚያ ለዚህ ነገር ያነሳሳኝንና ስለ ህዝቤ በተለይም ስለ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ሸክምን ሰጥቶ እያተጋኝ ያለውን ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፡፡ በጸሎትና በተለያዩ ድጋፎች ከጎኔ የቆሙትንም እግዚአብሔር ከጸባኦት ይባርካቸው እላለሁ፡፡
በብሎጉ ላይ የሚጻፉት ጽሁፎች በአብዛኛው ድነት ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ አልፎ አልፎ ከዚያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ለሌሎች ቅዱሳን ወንድሞችና እህቶች የሚጠቅሙ ተሐድሶአዊ መልዕክቶችም ይቀርባሉ፡፡ ለምሳሌ በድነት ዙሪያ ከሚቀርቡት መካከል ሚስጥረ-ድነት ፣ አስቸኳይ መልዕክት ፣ ከሲኦል የተላከ ደብዳቤ ፣ ንስሐ ገብተዋልን? የሚሉ  ይገኙባቸዋል፡፡ በፌስ ቡክ ላይ እንዲቀርብ ታስቦ የተሰሩ በጥበባዊ መንገድ ወንጌልን የሚናገሩ ጽሁፎችም አሉበት:: ለምሳሌ ለቪዛ ፈላጊዎች ፣ ነጻ የትምህርት ዕድል ፣ ክፍት የስራ ቦታ ፣ ዜና ማህደር ፣ የሰርግ ጥሪ… የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ከዚሁ የድነት መልዕክት ጋር የተያያዘ እና የክርስቲያን በዐላትን አስመልክቶ የተጻፉ መልዕከቶችም አሉ፡፡ ለምሳሌ ፋሲካ ፣ የገና መልዕክት ፣ ስለ ስቅለት ፣ ስለ ሰሞነ ህማማት ሲሆኑ በቀጣዩ ታንክስ ጊቪንግ ላይ እና የአዲሱ ዓመት መልዕክቶች እየተዘጋጁ ነው፡፡ የአበሻው ህብረተሰብ በዓለም ላይ ሁሉ የተበተነ እንደመሆኑ አንዳንድ በዐላት ሁለት ጊዜ የመከበር እድል አላቸው፡፡ ከዚህም የተነሳ እንደየ አውዱ እና የአገራቱ በዐል መሰረት፤ በተለይም በዌስተርን አገሮችና ከራሳችን ባህል አንጻር ተመጣጥነውና ታስቦ የቀረቡ መልዕክቶች ናቸው፡፡ ከዚሁም ጋር አንዳንዶቹ በውጪ አገር ተወልደው ያደጉ በመሆኑ፡ ከቋንቋ አንጻር  እንዳይቸገሩ ዋና ዋና የድነት መልዕክቶች በእንግሊዝኛ ጭምር ተጽፏል፡፡ ለምሳሌ urgent message , Don’t Delay ,the secret of Salvation….etc ሲሆኑ፡፡ በቀጣይም በኦሮምኛ /ቁቤ/ እና በእስፓኒሽ ቋንቋ ለማስተርጎም ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡ ይህም በተለይ በሰሜን አሜሪካ ብዙ ህዝብ ከመኖሩ አንጻር ነው ፡፡ በሌሎችም ቋንቋዎች ሁኔታው እንዳመቸ መጠን ለማድረስ ጥረት ይደረጋል፡፡
የቆዩ ክርስቲያኖችን በመንፈሳዊ ህይወታቸው ለማበረታታትና የበለጠ እንዲተጉ ለማስቻል የተጻፉ መልዕክቶችም አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ቀን ሳለ ፣ እግሬን አታጥብም ፣ አገልጋይና አገልግሎቱ ፣ ሰጥቶም ነስቶም ፣ ንገስባት ፣  የእግዚአብሔር አሳብ እና ስለ አራቱ ጨረቃዎች ከመጨረሻው ዘመን ጋር በማያያዝ ተጽፈው ቀርበዋል፡፡
ከዚህ ሌላ የኦርቶዶክስ ህዝባችንን ጥያቄ ከመፍታት አንጻር ሰው ሁሉ በዚህች ቤተክርስቲያን ስላለው የኑፋቄ አስተምህሮ እውነቱን እንዲያውቅ እና ለሌሎችም በጥሞና እንዲያስረዳ በማሰብ የተወሰነ ዕውቀት የሚያስጨብጡ ርዕሶችን በማንሳት በሰፊው ለመጻፍ ተሞክሯል፡፡ በዚህም አመርቂ ውጤት ታይቷል፡፡ ለምሳሌ ፡- ስንት አይነት መጽሐፍ ቅዱስ አለ? የሚል ከአዋልድ መጽሐፍት ጋር ተያይዞ የቀረበ ፣ አማላጅነት የሚል  ስለ ቅዱሳን ምልጃ ፣ የቅዱሳን መላዕክት ድርሻ ፣ ስለ ዝክር ፣ የሙታን ተስካር ፣ ስለ ካህናት ስልጣን ፣ ..ወዘተ የቀረበ ፤ በቀጣይ ስለ ቀኖና ና ዶግማ ፣ ሚስጥረ ቁርባን ፣ ጾም በሚል ርዕሶች በተከታታይ የሚቀርቡ ትምህርቶች ተዘጋጅተዋል፡፡
እስካሁን የወንጌል መልዕክቶችንና ፣ ሌሎች ተያያዥ ትምህርቶችን በፌስ ቡክ ፣ በኢ-ሜይል ፣ በጉግል ፕላስ ፣ በስልክ ቴክስቶችና  በቫይበር እየቀረቡ ያሉ ሲሆን፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች መልዕክቱን እያነበቡ እንደሆነ የሚቀርበው ዘገባ ያሳያል፡፡ በአንባቢያን መከታተያ ብሎጉ ላይ እንደሚያሳየው እስካሁን በ24 የተለያዩ አገራት ላይ በዓለም ዙሪያ ጽሁፎቹ ደርሰው እየተነበቡ ነው እነዚህም በአሜሪካ ፣ ኢትዮጵያ፣ ካናዳ ፣ እንግሊዝ፣ ኩዌት ፣ ባህሬን፣ ኔዘርላንድ፣ ሱዳን፣ ፈረንሳይ፣ ፖላንድ፣ ዩክሬን ፣ ግብጽ፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ብሩንዲ ፣ የመን፣ ጣሊያን፣ ኤርትራ፣ ኖርዌይ፣ ሀንጋሪ፣ ኬንያ ፣ ሩማንያ እና ሳውዲ አረቢያ ናቸው፡፡ ለወገኖቻችሁ የሚደርሳችሁን መልዕክት እያነበባችሁ ወደ ተለያየ ዓለም በመላክ የተጋችሁትን ሁሉ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ፡፡ እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ 2.1 ቢሊዮን ሰው የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንደሆነ በ2014 ላይ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በኦክቶበር 3, 2013 እንደወጣው መረጃ ደግሞ ከ 500 ሚሊዮን በላይ የሆነ ህዝብ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ነው ፡፡ ይህ ማለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በማቴዎስ ወንጌል 28፡ 18-20 እና ማርቆስ 16፡15 ‹‹ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ና ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ንገሩ ብሎ እንዳዘዘ ….›› በትዕዛዙ መሰረት ይህን ለመተግበር ህዝቡ የት ነው ያለው ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ይኸው ከላይ እንደተገለጠው ከ 7 ቢሊዮን የዓለም ህዝብ ውስጥ ከ 2 ቢሊዮን በላይ የሚሆነውን ኢንተርኔት ላይ ነው የምናገኘው ማለት ነው ፡፡ የዳኑ ሰዎች ምን ያህሉ በዚያ ውስጥ እንዳሉ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ለማንኛውም ይህን መንገድ ተረባርበን ካልዋጀነው ሌሎች ገብተው ህዝቡን  ይዘርፉብናል፡፡
በዚህ አገልግሎት እሰካሁን በፌስቡክ  12 ያህል ግሩፖች ላይ መልዕክት በየሳምንቱ የሚደርስ ሲሆን በመጀመሪያው ግሩፕ 3,792 አባል አሉት/ መዝሙሮችና የመዝሙር ግጥም ለማቅረብ የተሰበሰበ ስብስብ ነው፡፡/ 2ኛው 46 / በአሜሪካን አገር የሚገኙ አበሻ የኮሌጅ ተማሪዎች ስብስብ ነው፡፡ /፣ 3ኛው 326 ገደማ ነው / በአንድ የአረብ አገር ላይ ያሉ ለመጸለይ እና ርዕሶችን ለመለዋወጥ የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ /፣ 4ኛው 2,311 ሲሆኑ / ኢትዮጵያ ላይ ቪዥን ያነገቡ ናቸው፡፡ /፣ 5ኛ 1,583 ገደማ ሲሆኑ እነዚህ አባላት በኢትዮጵያ ስላለው የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ትኩረት አድርገው የሚጻፉ ናቸው፡፡ 6ኛ 20 አባላት የሚሆኑ ናቸው፤ በአብዛኛው አማኞች አይመስሉም፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ ዓላማ ያላቸው ይመስላል፣ 7ኛ 7,657 ያህል አባላት ያሉበት ና ዓላማቸውም ወንጌል ነክ የሆነ ግሩፕ ነው፡፡ 8ኛ 149 ያህል ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ቤተክርስቲያን ወጣቶች የመሰረቱት እና እርስ በርስ የሚተናነጹበት ድረ ገጽ ነው ፣ 9ኛ በዓለም ላይ ያሉ ሴቶች ላይ መንፈሳዊ ራዕይ አንግቦ የተመሰረተ ግሩፕ ነው፤ በአንዲት ነጭ አገልጋይ ይመራል፡፡ ከዚህ በተረፈ ያለው 3ት ያህል ገጾች እኔ የመሰረትኳቸው ናቸው ፡፡ አንደኛው ላይ ከ475 በላይ አባላት ያሉበት ኢየሱስ ያድናል የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚል ከግዕዝ ጋር የተቀላቀሉ የድነት መልዕክቶች የሚወጡባቸው ና በመጠይቅ መልክ የወንጌል መልዕክት የሚቀርብባቸው ናቸው፡፡ ሶስተኛው ትምህርታዊ ድረ ገጽ ነው ፤ ሪፎርሜሽን ባይብል ስኩል ይባላል፡፡ ጠንከር ያሉ ህይወት ተኮር መንፈሳዊ ትምህርቶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በተጨማሪ በጉገል ፕላስ ላይ 9,326 ተመልካቾች/ views/ ና 29 ተከታዮች /followers/ አሉ፡፡ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ የተዘጋጀ የድነት መልዕክት ይቀርብበታል፡፡ ተሐድሶ ቶውት በሚለው ብሎግ 51 ያህል ልዩ ልዩ መልዕክቶች እሰካሁን ቀርበዋል፤  13068 ጊዜ ተነበዋል ከላይ እንደተገለጸው በቁጥር አንድ የተነበበው 10060 ገደማ ሰሜን አሜሪካ  ውስጥ ሲሆን፤ 1129 በኢትዮጵያ እና ሌሎች አገሮች በቅደም ተከተላቸው ይከተላሉ፡፡ በብሎጉ ላይ የተወሰኑ የቪዲዮ መልዕክቶች እና ትምህርቶች በክርስቶስ አምነው በዳኑ መርጌታዎችና መምህራን ተዘጋጅቶ  ለህዝብ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡ አንዳንድ ጽሑፎችም እንደ አስፈላጊነቱ  ከሌሎች አገልጋዮች ማስታወሻ ላይ ተወስዶ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ወደ ፊትም እንደ ሁኔታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ አብዛኛው መልዕክቶች ለሰዎች የሚደርሱት በሞባይላቸው ላይ ቴክስት በማድረግ ሲሆን እስካሁን ከ360 በላይ መልዕክት አድራሾች እና መልዕክት ተቀባዮች ቁጥር በእኔ ሞባይል ውስጥ አሉ፡፡ በቫይበር የሚጠቀሙ እና መልዕክት የሚደርሳቸው 268 ግለሰቦች ሲሆኑ ከ60 በላይ የሚሆኑ ቢያንስ ከ10 እስከ 25 የሚደርሱ አባላት ያሉባቸው ግሩፖች ውስጡ አሉ፡፡ ለእነርሱም በተመሳሳይ በየ ግሩፑ መልዕክት ይላክላቸዋል ፡፡ በታማኝነት አንብበው ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መልዕክቱን የሚያጋሩ ብዙ አሉ፡፡ ጌታ ልፋታችሁን ቆጥሮ ዘመዶቻችሁንና ጓደኞቻችሁን ያትርፍላችሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ በርካታ የኢሜይል ላይ ደንበኞች አሉ ፡ ብዙ ጊዜ ሞባይሌ ላይ አማርኛ አልሰራልኝም ከሚል ጋር ተያይዞ ነው ኢሜይል አድራሻቸውን የሚልኩት፡፡ ሁሉንም ቴክኖሎጂዎች መጠቀም ለማይችል ደግሞ የደብዳቤ አገልግሎት ተዘጋጅቷል፡፡ በየትኛውም ስፍራ ላሉ ሰዎች የድነት ደብዳቤ በአድራሻቸው የመላክ አገልግሎት ነው ፡፡ በዚህም  አንዳንዶች ወደ ቤተሰቦቻቸው በመላክ ፣ለስራ አለቆቻቸው በመስጠት ድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡ ሁላችሁን ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ፡፡
እግዚአብሔር እንደረዳን እስካሁን በዚህ መልክ ተንቀሳቅሰናል፡፡ ዓለም ሁሉ ድኖ እስኪያበቃ ወይም ጌታ ተመልሶ እስኪመለስ ወንጌል መስበካችንን በአዳዲስ ሌሎች ስልቶችም እንቀጥላለን፡፡ቀደም ብለን  የጀመርነውን ይህንን የስርጭት ዘዴም በስፋት እንቀጥላለን፡፡ በተለይ በቀጣይ ሁሉም ክርስቲያን ቢያንስ ለ 10 ሰዎች ከቀረቡላቸው አማራጮች በአንዱ መንገድ ወንጌልን እንዲመሰክሩ ፤አልያም 10 ሰዎችን አድራሻ በመስጠት እንዲጸለይላቸውና እንዲመሰከርላቸው እንዲያደርጉ በስፋት ከአብያተ ክርስቲያናት ጋር በመቀናጀት ለመስራት ዕቅድ አለ፡፡ ለነፍሳት ለመጸለይ ሸክም ለተሰጣቸው ሰዎችም  ርዕሶችን በመስጠት በቤታቸው ሆነው ለነፍሳት እንዲተጉ ይደረጋል፡፡ በዚህ መልክ ለአገልግሎት የተለዩትን ሰዎች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ክርስቲያኖች መስካሪ የማድረግ ጥረት ይቀጥላል፡፡ በዚህ ሪፖርት ላይ ያልተገለጡ ሌሎች ዕቅዶችም አሉ፡፡ ጌታ በነገር ሁሉ ያግዘን ዘንድ መጸለይና በአስፈላጊው ነገሮች ሁሉ ከጎን በመቆም የወንጌል ማህበርተኝነታችንን እናሳይ፡፡ የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን፡፡
                                                               በጌታ አገልጋያችሁ ብንያም በፍቃዱ አቦዬ
                                                                         ከሜሪላንድ
                                                                              benjabef@gmail.com