Saturday, June 27, 2015

አፋልጉኝ !

    ልብ ብለው ያንብቡ፡፡ ምንም እንኳ ክርስቶስ  የዓለም መድኀኒት ሆኖ የጠፉትን በጎች ፍለጋ  ቢመጣም እሺ ብለው የታዘዙትና ያመኑተት ጥቂቶች ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ከመንግስቱ እርቀው ነው ያሉት፡፡ ስለሆነም ዋጋ የከፈለላቸውን እነዚህን  ተቅበዝባዥ ህዝብ ካሉበት ቦታ እየፈለጉ በወንጌል መልዕክት ወደ መንግስቱ ለሚያመጡ እውነት እላችሁዋለሁ ዋጋቸው አይጠፋም፡፡
                     የጠፉ ሰዎች ልዩ ምልክታቸው



·        1-   ሰላም የላቸውም ፣ ትርጉም ሌለው ኑሮ እየኖሩ እንደለ ያውቃሉ፣ በብዙ ጉዳይ ደስታ ከህይወታቸው ስለጠፋ ዘውትር ይጨነቃሉ አንዳንዶቹ እንደውም የክርስቶስን ወንጌል በግልጽ ይቃወማሉ፡፡
      '' መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ ከሰማይ የተሰጠ ስም ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ማንም የለም፡፡'' ሐዋ.4፡12 :: የሚለውን  ያልተረዱ ናቸው፡፡
 2-    ከሐጢያታቸው በንስሐ ከመመለስ ይልቅ ምኞታቸውን ለመፈጸም ሰበብ ያበዛሉ፡፡
 3-   ዓለምንና በዓለም ያለውን ነገር በመውደድ የተጠመዱ ናቸው፡፡
''  ወቀረበ ኢየሱስ ወተናገርሙ እንዘ ይብል ተውህበ ሊተ ኩሉ ኩነኔ ሰማይ ወምድር ሑሩ መህሩ ኩሉ አህዛብ እንዘ ታጠምቅዎሙ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ ወመህርወሙ ኩሉ ያዕቅቡ ዘአዘዝኩክሙ፡ ወናሁ አነ ምስሌክሙ በኩሉ መዋዕል እስከ ኅልቀተ ዓለም፡፡''  ወንጌል ዘ ማቴዎስ 28፡18-20
ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com

Wednesday, June 24, 2015

የትንሹዋ ነገር ቀን !

  ገና ከዘፍጥረት ጀምሮ  የሰው ልጅ ምድርን እንዲጠብቃትና እንዲንከባከባት ተልዕኮ ሲሰጠው እንመለከታለን፡፡ ሰዎች አሁን አሁን ስራን በተለያየ መልክ ሊሰሩት ይችላሉ፡፡ ቅጥርን የሚፈልጉ ሌሎች በሚሰሩት ነገር ውስጥ በመግባት የተወሰነ ነገር በማድረግ ገቢን ለራሳቸው ያገኛሉ፡፡ ገሚሶች ደግሞ የራሳቸውን ስራ ፈጥረው ይሰራሉ፡፡ የራስን  ስራ ፈጥሮ በመስራት ዙሪያ ዛሬ የተወሰነ ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡

  ስራን ፈጥሮ አብሮ መስራት ከብዙ ነገር አንጻር ጥቅሙ ሰፊ ቢሆንም ፡ቅድመ ዝግጅቶች ከሌሉበት ግን በዕውቀት ማነስ የሚበላሸው ነገር ሊበዛ ይችላል፡፡ አብሮ ለመስራት ምን አይነት ዕውቀት ነው የሚያስፈልገን?

1. በቅድሚያ ራዕይ ሊኖረን ይገባል፡፡

 ራዕይ ከምንሰራው ነገር በፊት መኖሩ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ስራውን በጋራ የሚሰሩት በተመሳሳይ ራዕዩ ያላቸው ወይም በዚያ ራዕይ የሚስማሙ  ናቸው ፡፡ የቢዝነስ ጣምራም ያ ነው፡፡ ከስራው በፊት የጋራ ስምምነት ያወጣሉ፤ ራሳቸውን ጨምሮ ወደፊት ስራው ላይ የሚጨመሩት ሰዎች በሙሉ የሚተዳደሩበት እና የሚገዙለት ሕግ ይሆናል፡፡ ይህም ወደፊት የሚነሱ ችግሮችን ለመቀነስ ያስችላል፡፡ በስራው ውስጥ ቸልተኝነትን ለማጥፋት ፣ ብሎም የእርስ በርስ ቅራኔ እንዳይፈጠር ለማድረግ ሁሉም የስራ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ ፣ የተሰጠውን ሀላፊነት እያንዳንዱ በተገቢው ሁኔታ እንዲወጣ ማድረግ እና ባልተሰሩ ስራዎች ላይ ተጠያቂነትን መለማመድ ወሳኝ ነገሮች ከሚባሉት ውስጥ ናቸው፡፡

2. ትንሽ የሚመስሉ ጅማሬዎችን ማክበር፡፡

  የእግዚአብሔር ቃል  የጥቂቱዋን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ዘካ.4፤10 እንደሚል፡ እጅግ የገዘፉ ራዕዮች እጅ ላይ ባሉ ጥቂት ነገሮች ሊጀመሩ ይችላሉ፡፡ እንደውም ብዙ ነገሮች በጅማሬ ጊዜ ላይሳኩ እና ላይስተካከሉ ቢችሉም፡  ዓላማው ትልቅ እስከሆነ ድረስ እና በነገሩ ላይ የእግዚአብሔር ፈቃድ እስካለበት ድረስ፡ መነሻ ካፒታሉ ትንሽ ቢሆንም ሊደንቀን አይገባም፡፡ ያለችውን ፣የተገኘችውን ይዞ መጀመር ከዚያም በትጋት መስራት ይገባል ፡፡

 3. ራዕይ ከየት እና እንዴት ይጀምራል?

 ሰዎች ሊሰሩ የሚያስቡትን ስራ ወይም አንድን ራዕይ ከሆነ ነገር ተነስተው ይጀምሩታል፡፡ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታ ሲሙዋሉላቸው ወይም  ለመነሻ ከሚሆን ጥቂት ነገር ተነስተው ፡፡ በዚህ ጉዳይ እሰኪ አንድ አንድ ነገሮችን ከዮሐንስ ወንጌል 6 ላይ እንመልከት፡፡ 
" ኢየሱስም ዓይኖቹን አንስቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊሊጶስን ፡- እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን ? አለው፡፡ ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ፡ ሊፈትነው ይህንን ተናገረ፡፡ '' ዮሐ.6፤ 5ና 6፡፡

   ከላይ እንደተጠቀሰው ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ ጠየቃቸው ፡፡ ‹ህዝቡን ለማብላት እንጀራ ከወዴት እንገዛለን?› በመሰረቱ እየመጣ የነበረው ህዝብ፡ ወንዶች ብቻ ተቆጥረው 5ሺህ ህዝብ ነበሩ፡፡ ሴቶችና ህጻናት ሲቆጠሩ 13 ሺህ ገደማ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ ነገሩን እነዚህን ሁሉ የመመገብ የራዕይ ጅማሬ ብለን ልናስበው እንችላለን፡፡ ረዕዩ ሲታይ በጣም ሰፊ እና ገና በሐሳብ ደረጃ ያለ ነገር ነው፡፡  ሰዎች አንድን ራዕይ ለመጀመር ከሐሳብ ቀጥሎ የሚያነሱት ጥያቄ አላቸው፡፡ እነዚያ ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተሙዋሉ ድረስ ምንም ነገር መጀመር ሊከብዳቸው ይችላል፡፡   ፊሊጶስና እንድርያስ በራዕይ ጅማሬ ላይ ሊነሱ የሚገባቸውን ሁለት ቁልፍ  ሐሳቦችን አንስተውልናል ፡፡

                ሀ. አንድን ነገር ለራዕዩ የሚያስፈልግ ነገር ሲሙዋላ መጀመር...? 

ፊሊጶስ፡- '' ፊሊጶስም እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኩዋ እንዲቀበሉ የ 200 ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም ብሎ መለሰለት፡፡ ቁ.7፡፡ በዚያን ጊዜ ከጌታ የተሰጣቸውን አንድ ፕሮጀክት ወይም ራዕይ ለመጀመር የሚያስፈልገውን መነሻ ካፒታል ነው አስልቶ የተናገረው፡፡ 200 ዲናር በጊዜው በጣም ብዙ ብር ነው፡፡ ነገሩን የበለጠ ለመረዳት ያህል፡ ጌታ ኢየሱስን አሳልፎ ለጠላቶቹ ለመስጠት ይሁዳ ከካህናት አለቆች ጋር የተደራደረበት ብር 30 ብር ነው፡፡ በዚህ ብር በዚያን ጊዜ እንጀራ ቀርቶ መሬት እንኩዋ የሚገዛበት ብር እንደነበረ  ከቃሉ መረዳት እንችላለን፡፡ጌታውን የሸጠበትን ገንዘብ በቤተ መቅደስ ሄዶ በተነ፤ ነገር ግን መሬት ገዙበት፤ ቦታውም አኬልዳማ ተባለ ፤የተባለው ነገር ነው፡፡ እንግዲህ 30 ብር በጊዜው እንዲህ ትልቅ ከነበረ፡ 200 ብር ምን ያህል ይሆናል? የፊሊጶስ ሒሳብ ለሰው አዕምሮ ትክክል ይመስላል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩትን ለመመገብ ይህን የሚያክል በጀት አስፈላጊ ነው ማለቱ፡፡

                      ለ. ራዕዩን በእጅ ላይ በተገኘው ነገር መጀመር......?

እንድርያስ፡-''..አምስት የገብስ እንጀራ እና ሁለት ዓሳ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል፡፡ '' ቁ.9 ፡፡ ይህ  ሁለተኛው የአማራጭ ሐሳብ ነው፡፡ ፈንድ ተፈላልጎ፡  አልያም በሆነ መንገድ ከሚገኝ ካፒታል መጀመር የማይቻል ከሆነ፡ ምናልባት እጃችን ካለው ጥቂት ነገር መጀመር ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ነገር ግን እጃችን ላይ ያለው ነገር ለምንም ካልሆነስ ነው ጥያቄው? ፐሮጀክቱ ያቀፈው ህዝብ በሺህ የሚቆጠር ፡ በእጃቸው ያለው መነሻ ካፒታል ደግሞ ለአንድ ለሁለት ሰው ብቻ የሚበቃ፡፡ 'ይህ ምን ይሆናል ? ' አለ እንድርያስ !

   በነገራችን ላይ በርካታ ራዕዮችና ውጥኖች ሳይሰራባቸው ተቀምጠው ያሉት፡ በነዚሁ ሁለት ግዙፍ ጥያቄዎች  ውስጥ ወድቀው ነው፡፡ መነሻ ካፒታል ሲታሰብ ፣ ለመነሻ የሚሆን ብር ሲጠበቅ አይሞላም፡፡ ስለዚህም ፈቀቅ ማለት አይቻልም፡፡ ቤሳ ቤስቲ የሌላቸው ሰዎች ከመሬት ተነስቶ 200 ዲናር ከየት ያመጣሉ? ሌላው ደግሞ እጃችን ላይ ያለው ነገር ለምንም የማይበቃ መሆኑ ነው ፡፡ በተለይም ከታሰበው ራዕይ ጋር ሲነጻጸር ማለቴ ነው፡፡ ጀምሩት ቢባል እየቆረሱ ድንገት ቢያልቅስ ? ፣ ጀምሮ መዋረድ አይሆንም ? አዕምሮ ያለው ሰው ይህንን ሊያደርግ ይችላልን ?  ስለዚህም ነው በሁለቱም ጎራ የተነሱት ሐሳቦች ብዙዎቻችንን ይወክላሉ ብዬ የማምነው፡፡ ሁለቱም ነገሮች ከባባዶች ናቸው፡፡ ሙሉ የፕሮጀክቱን መነሻ ካፒታል ማግኘትም ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ካላችሁ ነገር ጀምሩ ማለትም በሁዋላ ላይ የሚመጣውን መዘዝ በማሰብ የሚያንቀሳቅስ አይደለም፡፡ በዚህ ሁሉ የጌታ ሐሳብ ለመሆኑ ምንድን ነው?

     የጌታ ሐሳብ - ‹ ከየትን እንጂ በምንን አታስብ ! ›

 ታስታውሱ እንደሆነ  ሲጀመርም የጌታ ጥያቄ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን ? ነው እንጂ በምን እንገዛለን? የሚል አልነበረም፡፡ ለጌታ በምን? የሚለው አያስጨንቀውም፡፡ ስለዚህም ነው በምን? ን ትቶ ከየት? የሚለውን የጠየቀው፡፡ ሰው ደግሞ በምን? የሚለው ሳይመለስለት ከየት? ወደሚለው ቀጣይ ነገር ውስጥ መግባት አይፈልግም፡፡ ስለ ዚህም ነው ሳይጠየቁ ሒሳብ መስራት የጀመሩት ፡፡ ለተሰጠ ራዕይ ሁሉ የሰው አስተሳሰብ ይኸው ነው፡፡ በቅድሚያ እንዲመለስለት የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ ካልተመለሰለት በቀር መጀመር ይፈራል፡፡ ጌታ ደግሞ እርሱን ለእኔ ተወውና ከየት እንደሚገዛ ንገረኝ ይላል፡፡ በተለይ '' እራሱ ሊያደርገው ያለውን ነገር አውቆ ይህን አለ፡፡'' የሚለው ቃል አስደናቂ ነው፡፡ ምንም ወደ ሌላቸው ሰዎች ትልልቅ ራዕይ ሲያመጣ እርሱ አዋቂ ነው፡፡ እርሱ ሊያደርግ ያለውን ነገር ስለሚያውቅ ነው ፡፡ በቅድሚያ በጀቱን ሰጥቶ ሂዱና ህዝቡን  አብሉ!፤ ይህንና ይህን ስሩ! ቢለን መልካም ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደዚያ አይሆንም፡፡

  ለመሆኑ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገሮች ፡ማለትም ፊሊጶስ ካቀረበውና፡ እንድርያስ ካቀረበው ሐሳብ፡ ጌታ የትኛውን መረጠ ? ወይም ምን አደረገ ? የሚለውን ነገር ከቃሉ ላይ አብረን እንመልከት፡፡ '' ኢየሱስም ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉ አለ፤በዚያም ስፍራ ብዙ ሳር ነበረበት፡፡ወንዶችም ተቀመጡ ቁጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር፡፡ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ ፡አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ ፤ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡዋቸው፡፡ ''ቁ.11-12
  እንዳነበብነው እጃቸው ላይ ያለውን : ያውም የራሳቸው ያልሆነ ግን በመካከላቸው የተገኘ የአንድ ብላቴና እራትን ተጠቀመበት፡፡ አመስግኖ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፡፡ በአዕምሮአችን ውስጥ መሀል ላይ ቢያልቅስ? ፣ ባይዳረስስ? ....ወዘተ የሚሉ አሳቦች ይኖራሉ ፡፡ ነገር ግን እነርሱን  እንተዋቸው፡፡ ዝም ብለን ባለን ነገር እንጀምር፡፡ አርሱ አያሳፍረንም፡፡ በጣም መጠንቀቅ ያለብን ፡ መነሻ ላይ ማነው የተናገረኝ? የሚለው ላይ ብቻ ነው፡፡ራዕዩ የትኛውንም ያህል ትልቅ ይሁን  እግዚአብሔር ተናግሮን ከሆነ መፈጸሙ አይቀርም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ለህዝቡ ቆርሰው ማደል ጀመሩ ፤ አይናቸው እያየ ሁሉ እንደሚፈልገው መጠን ወስዶ ፣ጠግቦ ፣ የተረፈውን ቁርስራሽ 12 መሶብ ሞሉ፡፡ የኛ ጌታ እንደዚህ ነው ፡፡ የመጨረሻውን ውጤት ከመነሻህ ጋር ማመሳከር እስኪያዳግት ድረስ የሚባርክ አምላክ ነው፡፡ በጣም ትልልቅ ነገር የሰራባቸውን ሰዎች ምስክርነት መመልከት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ዎርልድ ቪዥን ዛሬ ላይ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ካፒታል ከመድረሱ በፊት፡ መነሻ ካፒታሉ ቦብ ፒየርስ የሚባል የድርጅቱ መስራች  በወንጌል ምክንያት የተሰደደችን አንዲት ብላቴና በጊዜው ከረዳበት አምስት /5/ የአሜሪካን ዶላር እንደተጀመረ ጋሽ በቀለ ስለ ዎርልድ ቪዥን በጻፈው መጽሐፉ ላይ ታሪኩን አስፍሩዋል፡፡

  የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ ድንገት በአንድ ወቅት የቆፈረው ጉድጉዋድ እርሱ ልጆቹ ከብቶቹ ጠጥተው ደግሞ ከ ብዙ ዘመን በሁዋላም  ሌላ ትውልድ ይጠጣው እንደነበረ በዮሐንስ 4 ላይ ካለው ታሪክ ላይ መረዳት ይቻላል፡፡ ከራሳችን ያለፈ ነገር ማሰብ : ትውልድ የሚጠጣው ዘመን ተሻጋሪ ስራ መፍጠር ይቻላል፡፡ በርካቶች በራሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን የከፈቱት ቢዝነስ ህብረተሰቡን የሚለውጥ፣ አገርን እንኩዋ የሚጠቅም ሆኖ ተገኝቱአል፡፡ ከእነሱ አጥር ያለፈ አሳብ ስለነበራቸው ነው፡ ለውጥ ሊያመጡ የቻሉት፡፡የቆረቆሩት ትምህርት ቤት፣ የህጻናት ማሳደጊያ ፣ የአዛውንቶች መጦሪያ ወይም የህክምና ማዕከል ወይም የስራ ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከሎችን ገንብተው የህዝብ ንብረት አድርገዋቸዋል፡፡ ኤሌክትሪክን ለዓለም አበርክቶ እንዳለፈው ሳይንቲስት ማለት ነው፡፡

  እኛ ክርስቲያኖች በእምነት የአብርሐም ልጅነታችንን እንቀበላለን፡፡ ከዚህ ጋር የአብርሐምን ሙሉ በረከት መቀበልም ሊያጉዋጉዋን ይገባል፡፡ የአብርሐም በረከት  እባርክሀለሁ ፡ ደግሞ ለበረከት ሁን፡፡ ዘፍ.12፡1-3 ፡፡ የሚል ሲሆን፡፡ ‹እባርክሃለሁ› ራስን በተመለከተ ቢሆንም ፡፡ ‹ለበረከት ሁን ›የሚለው ቃል ግን ለሌሎች መትረፍን የሚያመለክት ነው፡፡

    በስራ ጊዜ የሚገጥሙ እንቅፋቶች፡-

ሰዎች መንፈሳዊና ባለራዕይ ቢሆኑም ከችግር ነጻ  ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም የአስተዳደግ ሁኔታ፣ የልምድ እጦት፣ ሰስጋዊነት ፣ የአካባቢ ወይም የዓለም ተጽዕኖ እና በሰይጣን የሚነሳ ውጊያ ስላለ ነው፡፡አብሮ በመስራት ጊዜ እነዚህ ችግሮች ብቅ ሊሉ ይችላሉ ፤ ችግሮች በተለያየ መልክ መቼም ጊዜ ሊነሱ ቢችሉም በወቅቱ ምን ና እንዴት ማድረግ ካላወቅንበት ይባባስና የት ሊደርስ የነበረ ስራ ይፈርሳል፡፡ ችግሮች በጥቂቱ ራስ ወዳድነት ፣ ግትርተኝነት /መሸነፍ ያለመፈለግ/ ፣የሌላውን ሐሳብ ያለመቀበል እና የንቀት ስሜት፣ ስንፍና፣ ለወጡ ህጎችና ስምምነቶች ያለመገዛት፤ነገሮችን አርቆ አለማሰብ-ችኩልነት፣ በሌላሰው ላይ አድቫንቴጅ ለመምታት ማሰብ፣ የፍክክር ስሜት....ወዘተ ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ችግሮች ሲፈጠሩ ምን ማድረግ አለብን ? የሚለው ነው
  • ወንድሜ ከእኔ ይሻላል ማለትን ማሰብ ፊሊ.2
  •  አብርሐም ለሎጥ ቅድሚያ እንደሰጠ ለሌሎች ቅድሚያ መስጠት
  •  ቅንነትና ታማኝነትን ማዳበረ
  •  በስራው ላይ የባለቤትነት ሰሜት ሳይሆን ባለ አደራ እንደሆኑ ማወቅ
  •  በመነሻ ጊዜ የወጡትን ስምምነቶች ማክበር ፡ ሀላፊነትን ለመወጣትም ተግቶ መስራት ነው፡
  • መጽናት
  •  በእግዚአብሔር ፊት መጸለየ
  •  ብዙዎች ለተስማሙበት ነገር ተቃራኒ ያለመሆነ
  • ሌሎች ተሞክሮአቸውን በምክር መልክ እንዲለግሱ መፍቀድ 
ይህን ክፍል ለማጠቃለል ያህል ከመነሻው ጀምሮ ራዕይ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች ከመፍትሔያቸው ጋር ለማቅረብ ተሞክሩዋል፡፡ እግዚአብሔር በሚሰጠን ጸጋ እንበርታ፡፡ የተቀሩትን ነገሮች በሌላ ክፍል እንዳስሳቸዋለን፡፡

                                                                                       benjabef@gmail.com



Tuesday, June 16, 2015

ፀሎተ ሐይማኖት !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት ጸሎት! በኒቂያ ጉባኤ በ 325 ዓ.ም. የተደነገገ፡፡

ሁሉን በሚገዛ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በእንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፡፡

      ዓለም ሳይፈጠር የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡ እርሱም ከብርሐን የተገኘ ብርሐን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የሚሆን : የተፈጠረ ያይደል የተወለደ : በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሆነ ሁሉ በእርሱ የሆነ : በሰማይና በምድር ካለው ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የሌለ : ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛንም ስለማዳን ከሰማይ ወረደ : በመንፈስ ቅዱስም ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋን ለበሰ: ሰውም ሆነ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ: መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረም በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ በክብርም ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም፡፡

     ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት በሚሰገድለትና በሚመሰገን ጌታ ሕይወት ሰጭ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በነቢያትም በተነገረ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፡፡ በሁሉም ዘንድ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡ ለኃጢአትም ስርየት : በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡ የሙታን ትንሳኤንና የሚመጣውን ዓለም ሕይወት በተስፋ እንጠባበቃለን፡፡ አሜን፡፡


     እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶድካሳዊት ቤተክርስቲያንም የተቀበለችው እውነት ይህ በመሆኑ ምዕመናን ሁሉ እንዲረዱት ፣እንዲያጠኑት ማገዝ ይጠበቅብናል፡፡ ስለ እኛ የተሰቀለውንና የሞተውን ደግሞ ከሙታን ተለይቶ የተነሳውን ጌታ ባለማመንና ባለማወቅ ሲኦል እንዳይገቡ ሁላችን የምንችለውን ሁሉ ስለ ወንጌል እናድርግ !!!

ተጨማሪ ንባብ ከፈለጉ እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com


 እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ታማኝ አምላክ ነው ! ይህችን መዝሙር ተጋበዙ...

ጸሎተ ሐይማኖት !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት ጸሎት! በኒቂያ ጉባኤ በ 325 ዓ.ም. የተደነገገ፡፡

ሁሉን በሚገዛ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በእንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፡፡

      ዓለም ሳይፈጠር የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡ እርሱም ከብርሐን የተገኘ ብርሐን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የሚሆን : የተፈጠረ ያይደል የተወለደ : በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሆነ ሁሉ በእርሱ የሆነ : በሰማይና በምድር ካለው ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የሌለ : ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛንም ስለማዳን ከሰማይ ወረደ : በመንፈስ ቅዱስም ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋን ለበሰ: ሰውም ሆነ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ: መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረም በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ በክብርም ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም፡፡

     ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት በሚሰገድለትና በሚመሰገን ጌታ ሕይወት ሰጭ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በነቢያትም በተነገረ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፡፡ በሁሉም ዘንድ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡ ለኃጢአትም ስርየት : በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡ የሙታን ትንሳኤንና የሚመጣውን ዓለም ሕይወት በተስፋ እንጠባበቃለን፡፡ አሜን፡፡


     እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶድካሳዊት ቤተክርስቲያንም የተቀበለችው እውነት ይህ በመሆኑ ምዕመናን ሁሉ እንዲረዱት ፣እንዲያጠኑት ማገዝ ይጠበቅብናል፡፡ ስለ እኛ የተሰቀለውንና የሞተውን ደግሞ ከሙታን ተለይቶ የተነሳውን ጌታ ባለማመንና ባለማወቅ ሲኦል እንዳይገቡ ሁላችን የምንችለውን ሁሉ ስለ ወንጌል እናድርግ !!!

ተጨማሪ ንባብ ከፈለጉ እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com

     

Wednesday, June 10, 2015

ዜና ማህደር !

የጦር አዛዡን ስለ ታደገች ብላቴና !
ታሪኩ እውነተኛ እና ታላቁ መጽሐፍ ላይ ተመዝግቦ የሚገኝ ነው፡፡ ከስንት ጊዜ በፊት ሶርያውያን ከእስራኤል ጋር ባደረጉት ጦርነት ወቅት ሶረርያውያን አንድ ብላቴና ማርከው ወደ አገራቸው ወሰዱ፤ ንዕማን በተባለ የአገሩ የጦር አዛዥ ቤት እንድትሔድና ሚስቱን እንድታገለግል ትደረጋለች፡፡ በዚያም ሳለች ንዕማን ምንም የተከበረ፣ ጀግናና ጽኑ ሰው ቢሆንም ነገር ግን ለምጻም ስለነበር በጣም ታዝንለታለች ፡፡ ለእመቤትዋም '' ጌታዬ በሰማርያ ካለው  ከነብዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር አለቻት፡፡'' 2ነገስት 5፡3

እመBትዋም ይህንን መልካም ወሬ እንደሰማች ለባለቤትዋ ለንዕማን ትገግረዋለች ፡፡ ቀን ተቀጥሮ ና ተዘጋጅቶም ወደዚያው ያቀናል፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት ለምጹ ተፈውሶ ፣ ከእግዚአብሔር ውጪም ከእንግዲህ ሌሎች አማልከቶችን ላለመከተል ቃል በመግባት ወደ አገሩ በሰላም ይመለሳል፡፡ የዘመናት ችግሩና ጥያቄውም በዚያው ቀን ተመለሰላት፡፡

ከዚህች ትንሽ ብላቴና ምን እንማራለን?
  • የምታውቀውን ፈዋሽ ነብይ አስተዋወቀች፤
  • ያለችበት ሁኔታ: ምርኮኛ መሆን፣ ብላቴና መሆን፣ ሰው ቤት መሆን...ወዘተ ያላገዳት ሴት ነች፡፡
  •  እኛስ እንዴት ነን? ለሰው ልጆች ሁሉ መድኀኒት ስለ ሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ላለመናገር ሰበብና ምክንያት ይኖረን ይሆን?
                                                                                                                                                                    ከጦር አዛዡስ ሕይወት ምን እንማራለን?


  • በቅድሚያ የዚህ ችገር /ለምጽ/ ተ ነኝ ብሎ ማመኑ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ዛሬ በርካታ ሰዎች የብዙ ሱስና ሐጢያት ተጠቂ ሆነው ግን ምክንያት ና ሰበብ ያበጁለታል እንጂ ይህ ችግር አለብኝ ብለው በግልጽ አያምኑም፡፡ ስለዚህም ፈውሳቸው ይዘገያል፡
  •  ሌላው ደግሞ ምንም ትልቅ ባለስልጣን ቢሆንም ከትንሽ ልጅ ለመስማት መዘጋጀቱ እና የወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሰሙት እውነት ቶሎ ምላሽ የሚሰጡ ነዎት?
  •  ያደረገለትን እግዚአብሔርን አመስግኑዋል፤ ከእርሱም ውጪ ሌላ አማልክቶችን ላለመከተል ቃል ገብቶአል፡፡ሌሎች እንዳዳኑት አስመስሎ በግብዝነት አልቀረበም፡፡
ልብ ይበሉ፡ ዛሬም በፍጹም ልባችን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ብንቀርብ በስጋችን ካለ ከየትኛውም ዓይነት  ችግር እና በነፍሳችን ደግሞ ከዘላለም ሞት ይታደገናል ፡፡

                ኢየሱስ ክርስቶስ የስጋም የነፍስም ፈውስ ነው!!!

                           Click here fore more Teachings  http://tehadesothought.blogspot.com

Monday, June 8, 2015

ነጻ የትምህርት ዕድል !

በህይወትዎ በአጭር ጊዜ ለውጥን የሚያመጣ ትምህርት የቱ ነው ?

ከትምህርቱ በሁዋላ ከእርስዎ የሚጠበቀው ነገር ምንድን ነው ?

'' እነዚህን አስተምርና ምከር ፡፡ ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ  ቢሆን በትዕቢት ተነፍቶአል፡ አንዳችም አያውቅም፡፡ ''1ጢሞ. 6፡3

ከላይ እንደተጠቀሰው ፡- 1. መማር ያለብዎት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ጤናማ ቃል ሲሆን፡ ይህም ጌታችን በአካል ሲያስተምር የነበሩ ሐዋርያት ተከታትለው የዘገቡት ወንጌላትና ፡ መልዕክታትን ማንበብ ይጠበቃል፡፡ የእግዚአብሔር ሐሳብ የሰፈረው በመጽሐፍ ቅዱስ  ውስጥ ነው፡፡

                                 2. ትምህርቱን ከተረዱ በሁዋላ ማድረግ የሚጠበቅብዎት ነገር፡ እግዚአብሔርን ለመምሰል መለማመድ ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔርን መሆን ማለት ሳይሆን እርሱ እንደሚፈልገው እንደ ቃሉ ሆኖ መገኘት ነው፡፡

   መማር የሌለብን ትምህርት ምንድን ነው?

    ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የተጻፉ ብዙ የሰው ድርሰቶችና ገድላቶች ስላሉ፡ አራስዎን ከዚያ መጠበቅ አለብዎ፡፡ሲጀመር እግዚአብሔርን ለመምሰልና ለዘላለም ህይወት ሊጠቅሙን ቀርቶ ፡ጭራሹን የሚያጎድሉንና ከእውነት የሚያስቱ ናቸው፡፡ ሲቀጥል እውነተኝነታቸው በታሪክ ያልተረጋገጠላቸው እና ለምድራዊ ህይወታችን እንኩዋ የማይበጁን ናቸው፡፡

ሐዋርያቱ  ከሰበኩልን ስለ ጌታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ  ከሆነው ወንጌል  የሚለይ ወንጌል  የሚሰብክ ፡ የሰማይ መልዐክ እንኩዋ ቢሆን የተረገመ ይሁን፡፡ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን፡ ተብሎአል፡፡ ገላ.1፡8-9

 እውነተኛ  ንስሐ ይግቡ! መጽሐፍ ቅዱስዎን ያንብቡ!

ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራረያና ትምህርት ከፈለጉ በሚከተሉት አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡
                    0911472871 /0911154937/0911374255 ወይም benjabef@gmail.com
                  ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com


የመኖሪያ ቤት ምዝገባ !

‹‹ ልባችሁ አይታወክ ፤በእግዚአብሔር እመኑ፡ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፡፡ እንዲህስ ባይሆን ባልኩዋችሁ ነበር ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፡፡ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ፡ ወደ እኔም እወስዳችሁዋለሁ፡፡›› ዮሐ.14፡1-3

በስማችን የተመዘገበ የምድራዊ መኖሪያ ቤት ሊኖረንም ላይኖረንም ይችላል፡፡ ቢኖረንም በጣም ጥቂት ጊዜ የምንኖርበት ነው፡፡ እኛም ቢሆን ቤቱ ያልፋሉና፡፡ ትልቁ ጉዳይ በዘላለም ቤት በመንግስተ ሰማይ ቤት የሌለን እንደሆነ ነው፡፡

       ለዘላለም ቤት እንዲኖርዎ ምን ማድረግ አለብዎ?

1. የዘላለም መንገድ ፣እውነት እና ህይወት በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን!
   ቃሉ እርሱን ክርስቶስን ብንክደው እርሱም ይክደናል ይላል፡፡ 2 ጢሞ.2፡12

2. ከሐጢያትዎ ሁሉ በንስሐ ተመልሰው ፡ መልካም ፍሬን ማፍራት፡፡

3. በቀሪ ዘመንዎ በፍጹም ልብ ክርስቶስን ለመከተል መወሰን፡፡ ይህን ሲያደርጉ ህይወትዎ ይለወጣል፤ የዘላለም ቤትም በሰማይ ይዘጋጅልዎታል፡፡

ማስታወሻ፡-ይህንን መልዕክት ለሌሎች ሼር ያድርጉ! 
/በተጨማሪ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com  

Saturday, June 6, 2015

ክፍት የስራ ቦታ!

 እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ የፈቀደው ስራ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡-

''...ይህ የእግዚአብሔር ስራ እርሱ  በላከው  እንድታምኑ ነው፡ ...፡፡ '' ዮሐ.6፡29

'' እርሱ ''-የተባለው ሁሉን የፈጠረ አምላካችን እግዚአብሔር አብ ሲሆን  '' የተላከውም '' አንድያ ልጁ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው፡፡

የእኛ ድርሻ፡- በአባቱ ተልኮ ወደ ምድር በመምጣት፣ በቅድስት ድንግል ማርያም ማህጸን ተወልዶ፣ ተሰቅሎ ፣ ለሐጢያታችን ስርየት እንዲሆን ክቡር ደሙን አፍስሶ፣ ሞቶ፣ በሶስተኛው ቀን ተነስቶ ደግሞ በ 40ኛው ቀን ያረገውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማመን ነው፡፡

 ልብ ይበሉ ለእርስዎ የተዘጋጀልዎ የእግዚአብሔር ስራ በልጁ በክርስቶስ ማመን ነው ! በእርሱም የሚያምን መጽሐፍ እንደሚል የዘላለም ህይወትን ያገኛል ዮሐ.3፡16 ፡፡ ለምድራዊ ኑሮዎ ግን ምድራዊ ስራ መስራት ሐጢያት አይደለም፡፡

ለተጨማሪ ትምህርት ይህንን ይጫኑ  http://tehadesothought.blogspot.com

ለቪዛ ፈላጊዎች !

የተለያዩ ሰዎች ኑሮአቸውን ለማሻሻልና ለማሸነፍ  በርካታ መንገዶችን ተጠቅመው ከአገር ይወጣሉ፡፡ አንዳንዱ ህጋዊነትን ተከትሎ የሚፈጸም ሲሆን፡ በተቃራኒው ህጋዊነትን ባልተከተለ መንገድ ለብዙ እንግልትና ስቃይ እየተዳረጉ አገር የሚቀይሩም ዜጎች አሉ፡፡ ይህም በዋነኝነት ሁሉም ሰው የሚፈልገውን  የቪዛ ጥያቄ እንደሚፈልገው ስለ ማይፈቀድለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ቪዛ  የሚፈቀድበት የራሱ መስፈርትና አሰራር አለው፡፡

   ይህ ሲባል ግን ትክክለኛ ቪዛ ያገኙ ሰዎች የሚሄዱበት ምድር ችግር አይገጥማቸውም ማለት አይደለም፡፡ እዚሁ ዓለም እስከሆነ ድረስ የትም አገር ቢሆን የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው፡፡ አንደየ ቦታው ሁኔታ ግን ሊለያይ ይችላል፡፡

በእርግጠኝነት ቪዛ ሊያገኙበት የሚችሉበት፣ በሚሄዱበት አገርም ምንም አይነት ችግር የማይገጥሞዎት አንድ አገር ብቻ ነው፡፡ይህን ዕድል ለመጠቀም ከፈለጉ በጥንቃቄ ቀጣዩን መስፈርቶች ይከታተሉ፡፡

መጽሐፍ ሲናገር  ''...ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤....ሞት ከእንግዲህ አይሆንም ፡ኀዘንም ወይም ጩኸት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፡፡'' ራዕይ 21፡1-4፡፡ በዚህ አዲስ አገር ውስጥ ምንም ችግርና ሰቆቃ የሌለ ሲሆን ደስ በሚል ብርሐን ውስጥ ሰላምና ዕረፍት አግኝቶ ከዘላለም እሰከ ዘላለም ድረስ መኖር ያስችላል፡፡

ቪዛውን ታዲያ እንዴት ማግኘት ይቻላል?

የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቁ.16-21 ያንብቡ፡፡ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ይመኑ! እርሱም ስለ እኛ ሐጢያት የተሰቀለ፣ የሞተ፣ በሶስተኛውም ቀን የተነሳ ነው፡፡ ልክ  ስለ  እርሶ የሞተውንና  የተነሳውን  ክርስቶስን  አምነው  ንስሐ  ሲገቡ ፡ ስምዎ  በህይወት  መጽሐፍ  ላይ ይጻፋል፤  የመንግሰተ  ሰማይ  መግቢያ  ቪዛውን ም ይቀበላሉ፡፡

       ለጥንቃቄ
  • ይጠንቀቁ! ቪዛውን እኛ እንሰጣለን የሚሉ ክርስቶስ የማያውቃቸው ና ህጋዊውን መንገድ የማይከተሉ በርካታ ሐይማኖታዊ ድርጅቶችና አገልጋዮች አሉ፡፡ መንገዱ አንድ ብቻ ነው እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡ ዮሐ 14 ቁ.6፡
  •  ንስሐ ገብተውና ተዘጋጅተው ፣ በማመን ያገኙትን የመዳን ቪዛ ይዘው ጌታ እስኪገለጥ ድረስ በእምነት ጸንተው ይጠብቁ!
  •  ቃሉን /መጽሐፍ ቅዱስን/ ያንብቡ ፣ በየዕለቱም ይጸልዩ!
                      Click here  For more Teachings http://tehadesothought.blogspot.com