ለብርሃነ ትንሳኤው እንኩዋን አደረሳችሁ!
'' ወይቤሉን ፡ አትደንግፃ፡፡ ኢየሱስሃኑ፡ ናዝራዊ፡ተኀሥሡ፡ ዘተሰቅለ፡፡ ተንሥአ፡ ወኢሀሉ፡ ዝየስ፡ ወናሁ፡ መካኑ፡ ኀበ፡ ተቀብረ፡፡ ''
/እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፡ አትደንግጡ፡ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡ እርሱ ተነስቶአል፡ እዚህ የለም፡ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ፡፡/ ማርቆስ 16፤6
ጌታችን ፣ መድኀኒታችን ና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁላችን በደል እና ሐጢያት መከራን ተቀብሎ በመስቀል ላይ ከሞተ በሁዋላ ፡ በሶስተኛው ቀን ከሞት ተነስቶአል፡፡ ይህ ብርሃነ ትንሳኤው ነው በመላው ዓለም የፋሲካ በዐል ተብሎ የሚታወቀው ፡፡
ፋሲካ የስሙ ትርጉዋሜ ማለፍ ማለት ሲሆን፤ ይህም እስራኤላውያን ከ 430 በግብጽ በባርነት አገዛዝ ከነበሩበት አሰጨናቂ ዓመታት ነጻ የወጡበት ቀን ነው፡፡ በዚያም ቀን ምሽት በሁሉ ቤት ታርዶ የነበረው ጠቦት ፣ በበራቸው ጉበንና በመቃናቸው የለቀለቁት ደም ምሳሌነቱ ክርስቶስና የክርስቶስ ደም ነው፡፡ጌታችን እኛን ከሐጢያትና ከኩነኔ ሊያድነን ዋጋ ከፍሎአል፡፡ አሁን በአዲስ ኪዳን ዘመን ከ ዓለም ልንወጣ የምንችለው ደግሞ የአዲስ ኪዳኑን / የፋሲካውን በግ / በማመንና በመቀበል ሲሆን ፣ በቀራኒዮ በፈሰሰው ደሙም ከሚመጣው ቁጣ ማምለጥ እንችላለን፡፡ ደሙን በጉበኑ ባላደረገ ቤት ሁሉ ሞት እንደነበረ፡ በክርስቶስ ደም ያልነጻ እና የደሙ ማህተም በግንባሩ የሌለ ማንኛውም ሰው ከዘላለም ሞትና ፍርድ ማምለጥ አይችልም፡፡
እርሶም ዛሬ ከግብጽ / ከዓለም / ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ አምልጠው አውነተኛውን የክርስትና ህይወት ሊኖሩ የሚወስኑበት ጊዜ እንዲሆን እመኝልዎታለሁ፡፡ በዛሬዋ ቀን በመስቀል ላይ ስለ እርሶ ሞቶ የተነሳውን ጌታ ና መድሓኒት በልብዎ ውስጥ ስፍራ ይስጡት፡፡ እስቲ የቀረዎትን ዘመን ለሞተውና ለተነሳው ጌታ ሊሰጡት ዛሬ ይወስኑ! እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይረዳዎታል፡፡
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልዎ!!!
ማስታወሻ፡- ይህንን መልዕክት ፋሲካውን እያከበሩ ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻችን ሁሉ ሼር እናድርግ!
benjabef@gmail.com

No comments:
Post a Comment