እንኳን አደረስዎ !
‹‹በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል፡፡ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፣ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ፡፡›› መዝ.65፡11
ገና በዘፍጥረት ወራትንና ዘመናትን
ደግሞ ወቅቶችን እንድንለይ ብርሀናትን በሰማይ ያደረገልን እግዚአብሔር ነው፡፡/ዘፈፍ.1፡14 ነና 15/፡፡ እነሆም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዓመታቶች እየተቆጠሩ አለ፡፡
ያለፈው ዓመት ለእርሶ እንዴት ነበር ? አንዳንድ ጊዜ የሀዘን፣ የመከራ፣ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሌላ ዓመት ደግሞ ልንረሳቸው
የማንችላቸው ትልልቅ ስኬቶች በህይወታችን የሆኑባቸው ጊዜዎች ይሆኑልናል፡፡ የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር በሰላም ወደዚህ አዲስ
ዘመን አሸጋግሮናልና ክብር ምስጋን ለእርሱ ይገባዋል፡፡ ምናልባት ባለፈው ዓመት ሊሰሩ ፈልገው ያልሰሩት፣ ሊማሩ ፈልገው
ያለተሳካልዎ ቢሆን ወይም ሌሎች በእንጥልጥል ላይ ያሉ ዕቅዶች ቢኖርዎ ፤ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ዘነድሮ ያደርጉታል፡፡ ሁልጊዜ
መረሳት የሌለበት ነገር ግን በህይወታችን የፈለገውን ዓይነት ዕቅድ ቢኖረንም እንኳ ልንተገብር የምንችለው እርሱ ከፈቀደልን ብቻ
ነው ፡፡ ለዚህም ነው በቃሉ ላይ ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህንና ያንን እንደርጋለን በሉ የተባለው፡፡ያዕ.4፡15
ስለ መንፈሳዊ ነገርዎስ ሲያስቡ
ያላደረጉትና የሚቆጭዎት ነገር ይኖር ይሆን? እስኪ በዚህ ጊዜ ላይ ግን ቆም ብለው ያስቡ በቸርነቱ ዘመን የጨመረልዎትን ጌታ
አክብረው ለማለፍ ቀሪ ዘመንዎትን ይስጡት የሚያደርጉት ሁለት በጣም ቀላል ነገሮችን ነው፡፡ ይሁንና ይህንን በማድረግዎ
ዘላለምዎትን ሁሉ ይቀይራሉ፡፡
1ኛ-ንስሐ መግባት ፡- እስኪ
ቀጥለው እንዲህ ብለው ንስሐ ይግቡ ፡፡ 1ዮሐ.1፡9
- ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ባለፉት ዓመታቶች ሁሉ በቸርነትህ ስለሰጠኸኝ
ና ስላደረክልኝ ነገሮች ሁሉ አስቀድሜ አመሰግንሀለሁ፡፡ ይሁንና እኔ ግን ታማኝ ሆኜ አንተን የሚያስደስትህን ሁሉ አላደረኩም፡፡
በስህተት ና በድፍረት የሰራሁትን ሐጢያት ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከበደሌ ሁሉ አንጻኝ፡፡
አሜን፡፡
2ኛ- ማመን፡- ምን ብለው ነው
የሚያምኑት? ሮሜ. 10፡9-10
- ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር
ልጅ ነው ፤ እርሱ ስለ እኔ ሐጢያት ተሰቅሏል ፣ ሞቷል ፣ በ 3ኛው ቀን ተነስቷል ፡፡
መልካም ዘመን ይሁንልዎ !
ማስታወሻ ፡- ተጨማሪ ነገር
ማንበብ ይፈልጋሉ ? የሚቀጥለውን ሊንክ ክሊክ ያድርጉ