Saturday, August 15, 2015

ንስሐ ገብተዋልን ?

ንስሐ ገብተዋልን ?
/ሌሎች እንዲጠቀሙበት share ያድርጉ /
"ኢየሱስ ይሰብክ ወይበል፡ተነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት!" /ኢየሱስም መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመረ / ወንጌል ዘማቴዎስ 4፤17
ምን ብለው ነው ንስሐ የሚገቡት?
/ እስኪ ከዚህ በታች ያለውን የንስሐ ጸሎት ባሉበት ቦታ ሆነው ለተወሰነ ደቂቃ ከልብዎ ሆነው ይጸልዩ / ፡-
'' ጌታ ሆይ እኔ ኃጢያተኛ ነኝ፤ከልጅነት ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ ባለማወቅና በድፍረት የሰራሁትን ኃጢያት ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ጌታ ኢየሱስ ሆይ ስለ እኔ ሐጢያት መከራን እንደተቀበልክ ፣ደምህን እንዳፈሰስክ ና እንደሞትክልኝ እምናለሁ፡፡ ስለ ሐጢያቴም በፈሰሰው ደምህ ከበደሌ ሁሉ አንጻኝ ፤ልጅህም አድርገኝ፡፡ ከዛሬዋ ዕለት ጀምሬ አንተን የህይወቴ ጌታና አዳኝ አድርጌ አምኛለሁ ፣ ተቀብያለሁ፡፡በልቤም ላይ ንገስ! ስሜንም በህይወት መዝገብ ላይ ፃፍልኝ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡"
ይህንን ታላቅ የንስሐ ጸሎት ከጸለዩ በሁዋላ ባደረጉት ውሳኔ ፅኑ! በእምነትዎም እንዳይደክሙ መፅሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ያንብቡ፤ ዘውትርም ይጸልዩ፡፡ ህይወታችንን የሰጠነው ጌታ በነገር ሁሉ ከእኛጋር ይሆናል፤ይረዳንማል፡፡አሜን፡፡
ተጨማሪ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com

No comments:

Post a Comment