Sunday, November 9, 2014

አራቱ ጨረቃዎች / ክፍል -2/

                                      አራቱ ጨረቃዎች -ክፍል ሁለት

በክፍል አንድ ላይ እንደተመለከትነው ጨረቃዎች ወይም ጸሀይ ወይንም ከወዋክብቶች በሚያሳዩት ለየት ያሉ ምልክቶቻቸው ለእስራኤል እና ለዓለም የሚያሰተላልፉት ብርቱ መልዕክት እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በ ዘፍጥረት 1 ቁጥር 14 ላይ ሲናገር "እግዚአብሔርም አለ ቀንና ሌሊቱን ይለዩ ዘንድ ብርሀናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ለምልክቶች ፡ለዘመኖች ፡ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፡፡'' ቃሉ ላይ ከላይ እንደተመለከተው 'ለምልክቶች' ይላል....ይህ ማለት ብርሀናቱ የሰው ልጆችን ስለ አንዳች ጉዳይ ከ እግዚአብሔር ዘንድ ሊደረግ ስላለ ነገር እንዲጠቁሙ ና ምልክት እንዲሰጡ የሚናገር ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው የጌታችን የኢየሱስ ከክርስቶስ መምጫው ምልክቱን ከሚናገሩት መካከል እነዚህ ብርሀሃናት ዋነኞቹ ናቸው--"ከዚያች ወራት መከራ በኋላ ወዲያው ጸሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሀኗን አትሰጥም ፤ክዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ የሰማይ ሀያላትም ይናወጣሉ፡፡በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል::"/ 24 ቁ 29/፡፡

ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ 2፡17-20 ላይ እንደጠቆመው እግዚአብሄር በመጨረሻ ዘመን ከሚያደርጋቸው ነገሮች እና የጌታን ቀን መድረስ ከሚያመለክትበት ነገር ውስጥ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም መቀየራቸው ጉዳይ ነው፡፡ መቼም ይህ  ሁሉ ጉዳይ ዝም ብሎ ሊሆን አይችልም፡፡ በባለፉት ዘመናት በነበሩ ክስተቶችም በዓለም ዙሪያ ጉልህ ነገሮች ተፈጽመዋል፡፡

ስለዚህ ነው ከናሳ በላይ የጨረቃና የፀይሐን ጉዳይ በብርቱ መከታተል ተገቢ የሚሆነው፡፡ እግዚአብሔር ብርሀናቱን ምልክት አድርጓቸዋልና...የእነሱ ለውጥ በአየር መበከልና ለሌሎች ሰው ሰራሽ ተጽዕኖ አመጣው ከሚባለው ነገር በላይ ነው፡፡ሙቀትና ብርሀንን ከመስጠትም ያልፋል፡፡ ብዙ ጊዜ ወቅቶች ስለ መፈራረቃቸውና ከላይ የተዘረዘሩትን ጥቅሞች ስለሚሰጡበት ጉዳይ ላይ ብቻ ብናተኩር ለመጨረሻው ዘመን ሁኔታ የሚያስተላልፉትን መልዕክት ተረድተን ልንጠቀምባቸው አንችልም፡፡
ብርሀናቱ ላይ የሚሆነውን ክስተት ሁሉ ብንከታተል ግን እግዚአብሄር አምላክ በመጨረሻው ዘመን ሊጠቁመን ከሚፈልገው ና ሊያደርገው የወሰነውን ሐሳቡን እንዲሁም፣ስለ ዋናው የልጁ የጌታችን የኢየሱስ ከክርስቶስ መገለጥን ሁኔታ ብዙ ልናውቅ እንችላለን፡፡

ተጨማሪ ጥቅሶች፡- መዝ.104፡19 ፤ ኢሳ.13፡10፤ ራዕይ 6፡12 ፤ ሉቃ.21፡25 ማንበብ ይችላሉ፡፡

በሚቀጥለው ጊዜ እነዚህ ምልክቶች በተለያየ ጊዜ ሲከሰቱ የእኛ ድርሻ ከሕይወት ፡ ከትጋትና ወንጌልን ከመመስከር ደግሞ ጌታችንን ተዘጋጅቶ ከመጠበቅ አንጻር ከእግዚአብሄር ቃል እንማራለን፡፡ ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን፡፡ አሜን፡፡ እነሆ ጌታ ኢየሱስ በቶሎ ይመጣል፤

                                                                                                           benjabef@gmail.com

No comments:

Post a Comment