Sunday, November 2, 2014

አራቱ ጨረቃዎች / ክፍል-1/

                  አራቱ ወደ ደምነት  ተለውጠው የሚወጡ ጨረቃዎች   በ /2014 እና 2015 እ.አ..አ/



     በ 2014/15 እ.ኤ.አ. አራቱ ጨረቃዎች ወደ ደምነት  ተለውጠው እንደሚወጡ የአሜሪካ የጠፈር ምርምር መዐከል ባለፉት ጊዜያት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡የክስተቶቹ ጊዜያት በትንበያው መሰረት ሚያዚያ 15 እና ኦክቶበር  8 /2014 ሲሆን  ዕለታቱ የአይሁድ ፋሲካ እና የዳስ በዐል/feast of Tabernacle/ ላይ የሚውል ነበር ይህም ታሪካዊ ክስተት በትንበያው መሰረት በቅርቡ ተፈጽሙዋል፡፡ የቀሩት ሁለቱ ጨረቃዎች ደም ለብሰው የሚከሰቱበት ጊዜ የፊታችን አደሱ የ አውሮፓውያን ዓመት ኤፕሪል 14 እና ሴፕቴምበር 28 /2015 ነው ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህም በድጋሚ የአይሁድ ፋሲካ እና በታላቁ የዳስ በዐላቸው ዕለታት መሆኑ የሆነ አንድ ነገር ከእግዚአብሄር ዘንድ  የሚያመለክተው ነገር እንዳለ የሚያጠራጥር ነገር አይደለም፡፡
/በዚህ ጉዳይ በተለይ የ ጆን ሀጌን መጽሐፍ ቢያነቡ ጥሩ ነው፡፡/

ከዚህ በፊት ጨረቃ ወደ ደም ተለውጣ የወጣችባቸው ዓመት ነበሩ ለምሳሌ፡-
በ 1493-94 /እ..ኤ.አ./  ላይ ተከስቶ ነበር፡ በጊዜውም እስፔን የወደቀችበት፣ ለእስራኤላውያን የመከራቸው ጊዜ ነበር ፤ከዚህም ሌላ ኮሎመቦስ ታላቁዋን አሜሪካንን ያገኘበት ወቅት ሆኖ አለፈ፡፡
በ 1948-49 እ.ኤ.አ. ደግሞ በተከሰተበት ወቅት እስራኤል እንደ አገር ለዐለም ያወጀችበት ወቅት ነበር፡፡

  እ.ኤ.አ.በ 1967-68  ላይ ከጨረቃዋ ክስተት በሁዋላ እስራኤል በዐረቦች ከተከበበችበት ድንገተኛ ከበባ የ ስድስት ቀን ብርቱ ጦርነት አድርጋ በእግዚአብሄር እርዳታ በድል ያጠናቀቀችበት ወቅት ሆኖ አልፉዋል፡፡
አሁን ደግሞ ባለንበት በዚህ ጊዜ ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም የሆነ ነገር ግን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ሁኔታዎች አሉ፡፡ ለነገሩ ከ ኤፕሪል 15/2014 ክስተት በሁዋላ በእስራኤልና በዓለም ዙሪያ እየሆነ ያለውን ነገር መመልከት ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡

እስራኤል በሶሰቱ ወጣት ዜጎችዋ መገደል ምክንያት ለበቀል የወሰደችው ርምጃ እስካሁን ለበርካታ ወራት ያለቆመ ከመሆኑ ባሻገር ሺዎች የሞቱበት እና ከፍተኛ ውድመት የተደረገበት ነው፡፡በ ዓለም ላይ ቢሆን አይሲስ የሚባል አክራሪ የእስልምና ቡድን ተነስቶ ምድር በአሰቃቂ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡በዚሀም ላይ ኢቦላ የሚባል ከባድ ወረርሽኝ ተከስቶ ዐለመም ሁሉ ከፍተኛ ስጋት ላይ ነች፡፡እነዚህን ለ አብነት ያህል ይጠቀስ እንጂ እየተከሰቱ ያሉት ክፉ ሁኔታዎች በርካቶች ናቸው፡፡

ለመሆኑ ስለ ጨረቃ ወደ ደም መቀየር ክሰተት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ?ምን ትንቢትስ ተነግሩዋል.??......የሚሉትን ነጥቦች በ ቀጣይ ጊዜ እናነሳለን፡፡ ነገር ግን አሁን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ መጨረሻው ጊዜ ላይ እንዳለን አውቀን ራሳችንን በፊቱ በንስሀ እንድናቀርብ እመክራለሁ፡፡ እነሆ ጌታ በደጅ ነውና፡፡


                                                                                                      benjabef@gmail.com

No comments:

Post a Comment