Saturday, July 11, 2015

ከሲኦል የተላከ ደብዳቤ !

መጽሐፍ ሲናገር '' ወይቤ መጽሐፍ ኩሉ ዘየአምን ፡ ቦቱ፡ የሐዩ ፡፡/ በእርሱ የሚያምን አያፍርም፡፡'' ሮሜ.10፡11
/ በ ሉቃስ ወንጌል 16፡19-31 ላይ ያለውን ታሪክ አንድ ሰው በዚህ መልክ አቅርቦታል፡፡  


      ይድረስ በምድር ላይ  በአባቴ መኖሪያ ቤት ውስጥ እየኖራችሁ ላላችሁ አምስት የስጋ ወንድሞቼ፡፡ ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ ? ዛሬ ይህን ደብዳቤ ወደ እናንተ ልጽፍ ያነሳሳኝ ምክንያት አንድ ብርቱ ጉዳይ ላስታውቃችሁ ወስኜ ነው፡፡ እንደምታውቁት እኔ ወንድማችሁ በምድር ላይ በነበርኩ ጊዜ አንዳች ያልጎደለኝ  ሰው ነበርኩ፡፡ያማረኝን በልቼ .፣ያማረኝን ገዝቼ እኖር ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ስለ ሞት ካሰብኩ ፡ ከሞትኩ በኋላ ቅዱሳን ሰማዕታት ከሲኦል ይታደጉኛል የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ ነገር ግን እዚያ ስሔድ ያጋጠሙኝ እውነታዎች ፈጽሞ እንዳሰብኩት አልነበሩም፡፡ ሁለሉ ነገረር ተደበላለቀብኝ ልወጣው የማልችለው ሲዖል ውስጥ ራሴን አገኘሁት፡፡ ክፋቱ ደግሞ ፈጽሞ በምንም መንገድ ልወጣ የማልችል መሆኔን ስረዳ ይህንን ደብዳቤ ልጽፍላችሁ ወሰንኩ፡፡
·         በመጀመሪያ ሲኦልና ገነት ከመሞት በሁአላ አለ ሲባል ሰምታችሁ ከሆነ እውነት ነው፡፡ አለ!!!
·         በምድር ላይ እውነተኛ ንስሐ  ያልገቡ ና ትክክለኛ የህይወት ውሳኔን ያላደረጉ ሁሉ መጨረሻቸው ሲኦል ነው፡፡
·         አንድ ጊዜ ሲኦል ከተገባ በኋላ ጻድቃን ሰማዕታት ሊደርሱልን እንደማይችሉ ተረድቼአለሁ፡፡ ይህንንም እውነት ያወቅሁት ጻድቁ አባታችን አብርሐም ራሱን አነጋግሬው ነው፤ አላዛርን ሰድዶልኝ የምሰቃይበትን ነበልባል በጣቱ ጫፍ  ውሐ ነክሮ መላሴን  ጥቂት እንዲያበርድልኝ ተማጽኜው ነበር ፡ የእርሱ መልስ ግን በዚህ ያሉ ማናቸውም ወደዚያ ፡ ወዲያ በሲኦል ውስጥ ያሉ ወደዚህ እረፍት ቦታ እንዳይመጡ በመካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል ብሎ መልሶልኛል፡፡ የሉቃስ ወንጌል 16 ቁ.19-31 ፡፡ ስለዚህም ዝክር እየዘከራችሁ ከሆነ ፣ ወይም በስሜ የምታደርጉት ነገር ካለ ለመዳኔ አንዳች አይፈይድምና አትልፉ!!!
·         ከዚያም እናንተ ወደዚህ ስቃይ ስፍራ እንዳትመጡ እውነቱን ይነግራችሁ ዘንድ አላዛርን ወደ ምድር ወደ እናንተ እንዲልከው ተማጽኜው ነበር፡፡ ይህንም ያደረኩት ፈጽሞ ልታስቡት የማትችሉት ፡ነገር ግን እውነት የሆነ በዚህ ስላለ ፤ ሰው ከሞት ተነስቶ ካልነገራችሁ በቀር ላታምኑ ትችላላችሁ በሚል ነው፡፡ ጻድቁ አባታችን አብርሐም ግን እዚያ ያሉትን ነቢያት ና ሙሴ / የወንጌል መስካሪዎችን / ይመኑ እንጂ ሰው ከሞት ተነስቶ ቢመሰክርላቸውም አያምኑም አለኝ፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ወንጌል የሚነግሯችሁን ሰዎች አትናቁ! አውነት እነርሱ ጋር አለ፡፡ ከመሞታችሁ በፊት ምርጫችሁን አስተካክሉ፡፡ ምናልባት ሲኦል የሚያስገባችሁ መንገድ ላይ ከሆናችሁ ራሳችሁን  መርምሩ፡፡ እውነት የት እንደሆነ ፈልጉ፡፡ የሰው ይሉኝታ አይሰራችሁ፡፡ እዚህ ከመጣችሁ ስለእናንተ ማንም የሚሟገት የለም፡፡ በህይወት ሳላችሁ የመረጣችሁት ውሳኔ ነው የሚሰራው፡፡
·         በመጨረሻም የምጠይቃችሁ ነገር በተቻላችሁ መጠን ሁሉ ለዘመድ አዝማድ ፤ለጓደኞቻችሁ እና በዙሪያችሁ ላለ ህዝብ ሁሉ ይህንን እውነት አሳውቁ! ሁላችሁን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የሰራውን የዘላለም መዳን አምናችሁ ለመንግስቱ ያብቃችሁ፡፡

 '' የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ……አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ ፡፡ሰባኪው ከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል፡፡''  መክብብ 12፡1 ና 6-8


 NOTE:- እባክዎ እውነትን አብረን እንመስክር !!መልዕክቱን ለሌሎች ይላኩላቸው፡፡

No comments:

Post a Comment