Wednesday, July 1, 2015

ስለ አዲሱ መድኃኒት ምን ያህል አውቀዋል?

አዲስ መድኀኒት !

በዓለም ላይ የተወሰኑ በሽታዎች እስካሁን በምርምር መድኃኒት ሊገኝላቸው አልቻለም ፡፡ በዚህ ምክንያት ቁጥራቸው ጥቂት የማይባሉ የዓለም ህዝቦች በስቃይና በእንግልት ላይ ይገኛሉ፡፡መድሐኒት የተገኘላቸውም በሽታዎች ቢሆኑ ከበሽታው ቶሎ አለመገኘት፣ ከመድሐኒት አወሰሳሰድ ችግር እና ጊዜያቸው ባለፈባቸው መድሐኒቶች ችግር የተፈለገውን ውጤት እያመጣ አይደለም፡፡

ከበሽታዎች ሁሉ በጣም የከፋው የነፍስ ህመም ነው፡፡ ምንም እንኩዋ መድሐኒቱ ከተገኘ የቆየ ቢሆንም ብዙዎቹ ባለመውሰደቸው ምክንያት እስካሁን በነፍሳቸው እንደታመሙ ናቸው፡፡በአሁኑ ወቅት  በዓለም ላይ 3.6 ቢሊዮን የሚሆነው ህዝብ ስለዚህ መድሐኒት አልሰማም ተብሎ ይገመታል፡፡ የመድሐኒት እጥረት የለም ፤ግን መድሐኒቱን የሚሰጥ እና የሚያስተዋውቅ ባለሙያ እጥረት አለ፡፡

  ነፍስን እስከወዲያኛው ስለሚያሰቃየው ና መንስኤ ስለሆነው ሐጢያት ታላቁ መጽሐፍ እንደዚህ ይላል'' በበደላችሁና በኀጢያታችሁ ሙታን ነበራችሁ፡፡ ኤፌ.2፡1 ደግሞ '' ሁሉ ሐጢያትን ሰርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል'' ሮሜ.3፡23:: ይሁንና ለሐጢያት ደግሞ መድሐኒት ተገኝቶለታል፡፡ መድሐኒቱም ስለ እኛ የተሰቀለውና የሞተው ደግሞ የተነሳው  መድሐኒአለም ነው፡፡

የመድሐኒቱ አወሳሰድ

መጀመሪያ ሐጢያትን ሁሉ መናዘዝ ነው፡፡'' ኀጢያት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም ፡፡ በኀጢያታችን ብንናዘዝ ኃጢያታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡ '' 1ዮሐ.1፡9፡፡ ሐጢያትን ሁሉ የሚያነጻ ደም በቀራንዮ መስቀል ላይ ፈሱአል፡፡ ታዲያ እርሶ ንስሐ ገብተዋልን?

በመቀጠልም ስለ እኛ የሞትውንና የተነሳውን መድሐኒት ክርስቶስን ማመን ነው፡፡ የመዳን ቀን አሁን ነው!































No comments:

Post a Comment