ልብ ብለው ያንብቡ፡፡ ምንም እንኳ ክርስቶስ የዓለም መድኀኒት ሆኖ የጠፉትን በጎች ፍለጋ ቢመጣም እሺ ብለው
የታዘዙትና ያመኑተት ጥቂቶች ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ከመንግስቱ እርቀው ነው ያሉት፡፡ ስለሆነም
ዋጋ የከፈለላቸውን እነዚህን ተቅበዝባዥ ህዝብ ካሉበት ቦታ እየፈለጉ በወንጌል መልዕክት ወደ መንግስቱ ለሚያመጡ
እውነት እላችሁዋለሁ ዋጋቸው አይጠፋም፡፡
የጠፉ ሰዎች ልዩ ምልክታቸው
· 1-
ሰላም የላቸውም ፣ ትርጉም ሌለው ኑሮ እየኖሩ
እንደለ ያውቃሉ፣ በብዙ ጉዳይ ደስታ ከህይወታቸው ስለጠፋ ዘውትር ይጨነቃሉ አንዳንዶቹ እንደውም የክርስቶስን ወንጌል በግልጽ
ይቃወማሉ፡፡
'' መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ ከሰማይ የተሰጠ ስም ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ማንም የለም፡፡''
ሐዋ.4፡12 :: የሚለውን ያልተረዱ ናቸው፡፡
2-
ከሐጢያታቸው በንስሐ ከመመለስ ይልቅ ምኞታቸውን ለመፈጸም ሰበብ ያበዛሉ፡፡
3-
ዓለምንና በዓለም ያለውን ነገር በመውደድ የተጠመዱ ናቸው፡፡
'' ወቀረበ ኢየሱስ ወተናገርሙ እንዘ ይብል ተውህበ ሊተ ኩሉ ኩነኔ ሰማይ ወምድር ሑሩ መህሩ ኩሉ
አህዛብ እንዘ ታጠምቅዎሙ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ ወመህርወሙ ኩሉ ያዕቅቡ ዘአዘዝኩክሙ፡ ወናሁ አነ ምስሌክሙ
በኩሉ መዋዕል እስከ ኅልቀተ ዓለም፡፡'' ወንጌል ዘ ማቴዎስ 28፡18-20
ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com
No comments:
Post a Comment