Wednesday, June 10, 2015

ዜና ማህደር !

የጦር አዛዡን ስለ ታደገች ብላቴና !
ታሪኩ እውነተኛ እና ታላቁ መጽሐፍ ላይ ተመዝግቦ የሚገኝ ነው፡፡ ከስንት ጊዜ በፊት ሶርያውያን ከእስራኤል ጋር ባደረጉት ጦርነት ወቅት ሶረርያውያን አንድ ብላቴና ማርከው ወደ አገራቸው ወሰዱ፤ ንዕማን በተባለ የአገሩ የጦር አዛዥ ቤት እንድትሔድና ሚስቱን እንድታገለግል ትደረጋለች፡፡ በዚያም ሳለች ንዕማን ምንም የተከበረ፣ ጀግናና ጽኑ ሰው ቢሆንም ነገር ግን ለምጻም ስለነበር በጣም ታዝንለታለች ፡፡ ለእመቤትዋም '' ጌታዬ በሰማርያ ካለው  ከነብዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር አለቻት፡፡'' 2ነገስት 5፡3

እመBትዋም ይህንን መልካም ወሬ እንደሰማች ለባለቤትዋ ለንዕማን ትገግረዋለች ፡፡ ቀን ተቀጥሮ ና ተዘጋጅቶም ወደዚያው ያቀናል፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት ለምጹ ተፈውሶ ፣ ከእግዚአብሔር ውጪም ከእንግዲህ ሌሎች አማልከቶችን ላለመከተል ቃል በመግባት ወደ አገሩ በሰላም ይመለሳል፡፡ የዘመናት ችግሩና ጥያቄውም በዚያው ቀን ተመለሰላት፡፡

ከዚህች ትንሽ ብላቴና ምን እንማራለን?
  • የምታውቀውን ፈዋሽ ነብይ አስተዋወቀች፤
  • ያለችበት ሁኔታ: ምርኮኛ መሆን፣ ብላቴና መሆን፣ ሰው ቤት መሆን...ወዘተ ያላገዳት ሴት ነች፡፡
  •  እኛስ እንዴት ነን? ለሰው ልጆች ሁሉ መድኀኒት ስለ ሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ላለመናገር ሰበብና ምክንያት ይኖረን ይሆን?
                                                                                                                                                                    ከጦር አዛዡስ ሕይወት ምን እንማራለን?


  • በቅድሚያ የዚህ ችገር /ለምጽ/ ተ ነኝ ብሎ ማመኑ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ዛሬ በርካታ ሰዎች የብዙ ሱስና ሐጢያት ተጠቂ ሆነው ግን ምክንያት ና ሰበብ ያበጁለታል እንጂ ይህ ችግር አለብኝ ብለው በግልጽ አያምኑም፡፡ ስለዚህም ፈውሳቸው ይዘገያል፡
  •  ሌላው ደግሞ ምንም ትልቅ ባለስልጣን ቢሆንም ከትንሽ ልጅ ለመስማት መዘጋጀቱ እና የወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሰሙት እውነት ቶሎ ምላሽ የሚሰጡ ነዎት?
  •  ያደረገለትን እግዚአብሔርን አመስግኑዋል፤ ከእርሱም ውጪ ሌላ አማልክቶችን ላለመከተል ቃል ገብቶአል፡፡ሌሎች እንዳዳኑት አስመስሎ በግብዝነት አልቀረበም፡፡
ልብ ይበሉ፡ ዛሬም በፍጹም ልባችን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ብንቀርብ በስጋችን ካለ ከየትኛውም ዓይነት  ችግር እና በነፍሳችን ደግሞ ከዘላለም ሞት ይታደገናል ፡፡

                ኢየሱስ ክርስቶስ የስጋም የነፍስም ፈውስ ነው!!!

                           Click here fore more Teachings  http://tehadesothought.blogspot.com

No comments:

Post a Comment