በህይወትዎ በአጭር ጊዜ ለውጥን የሚያመጣ ትምህርት የቱ ነው ?
ከትምህርቱ በሁዋላ ከእርስዎ የሚጠበቀው ነገር ምንድን ነው ?
'' እነዚህን አስተምርና ምከር ፡፡ ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን በትዕቢት ተነፍቶአል፡ አንዳችም አያውቅም፡፡ ''1ጢሞ. 6፡3
ከላይ እንደተጠቀሰው ፡- 1. መማር ያለብዎት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ጤናማ ቃል ሲሆን፡ ይህም ጌታችን በአካል ሲያስተምር የነበሩ ሐዋርያት ተከታትለው የዘገቡት ወንጌላትና ፡ መልዕክታትን ማንበብ ይጠበቃል፡፡ የእግዚአብሔር ሐሳብ የሰፈረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው፡፡
2. ትምህርቱን ከተረዱ በሁዋላ ማድረግ የሚጠበቅብዎት ነገር፡ እግዚአብሔርን ለመምሰል መለማመድ ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔርን መሆን ማለት ሳይሆን እርሱ እንደሚፈልገው እንደ ቃሉ ሆኖ መገኘት ነው፡፡
መማር የሌለብን ትምህርት ምንድን ነው?
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የተጻፉ ብዙ የሰው ድርሰቶችና ገድላቶች ስላሉ፡ አራስዎን ከዚያ መጠበቅ አለብዎ፡፡ሲጀመር እግዚአብሔርን ለመምሰልና ለዘላለም ህይወት ሊጠቅሙን ቀርቶ ፡ጭራሹን የሚያጎድሉንና ከእውነት የሚያስቱ ናቸው፡፡ ሲቀጥል እውነተኝነታቸው በታሪክ ያልተረጋገጠላቸው እና ለምድራዊ ህይወታችን እንኩዋ የማይበጁን ናቸው፡፡
ሐዋርያቱ ከሰበኩልን ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆነው ወንጌል የሚለይ ወንጌል የሚሰብክ ፡ የሰማይ መልዐክ እንኩዋ ቢሆን የተረገመ ይሁን፡፡ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን፡ ተብሎአል፡፡ ገላ.1፡8-9
እውነተኛ ንስሐ ይግቡ! መጽሐፍ ቅዱስዎን ያንብቡ!
ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራረያና ትምህርት ከፈለጉ በሚከተሉት አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡
0911472871 /0911154937/0911374255 ወይም benjabef@gmail.com
ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ http://tehadesothought.blogspot.com

No comments:
Post a Comment