ዕለቱ ማክሰኞ በቨርጂንያ ሳምንታዊ ጸሎት የሚደረግበት ዕለት ነው ይህ የኦክቶበር 2018 ማስታወሻ ነው። ቀን ቀደም ብለን ሻይ ስንጠጣ S.Backs ላገኘነው ከኢትዮጵያ ከመጣ ሳምንት ላልሞላው ወንድም መሰከርንለት ዘላለም በግል ስራ የሚተዳደር ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው ነው የተነጋገርነውን ነገር ሳንቋጭ የአክስቱ ልጅ መጥታ ወሰደችው ደግነቱ አድራሻ ተቀያይረናል። ልቡ ተከፍቶ ስለ ወንጌል እውነት የሰማ ሰው ነው። ጸሎት ቤት እንደገባን አንድ ስልክ ተደወለልኝና ወጣ ብዬ አናገርኩ አንድ እህታችን አዲስ ሰው ወደ እኔ ልትልክ ፈልጋ ስለነበር ይህንኑ ለማስታወቅ ነው። በሰጠሁት ቁጥር መሠረት በነጋታው ተደወለልኝ። ሄሎ! ሐናን እባላለሁ አለች አንድ ሴት ..ተቀጣጠርንና ስልኩን ዘጋሁ። የቀጠሮአችን ቀን ዛሬ ሐሙስ ይህንን በምጽፍበት ቀን ላይ ነበር። ሐናን ቤተክርስቲያን ድረስ መጣች የዛሬ ሰባት ወር ገደማ ከሆነው ታሪክ ጀመረችልኝ። አንድም ክርስቲያን ከሌለበት ቤተስብ ነው የተወለደችው ኦርቶዶክስ እምነት የሚከተል ሰው ጋር ተጋብታ ልጆች ወልደው በአሜሪካን አገር መኖር ከጀመሩ ጥቂት ዓመታት አልፈዋል። አንድ ቀን በህልሟ ያየችውን አጫወተችኝ የመጨረሻ ሰዓት ይመስለኛል ጠቅላላ ጀለቢያ የለበሱ እና የጠመጠሙ ሰዎች በቅጽበት መሬት በትልቁ ተከፍቶ ሲገቡ አየኋቸው እኔ ምንም የለበስኩት ነገር አልነበረም፤ የቆምኩባት ቦታ ትንሽዬ አራት መዐዘን ቀርታለች። አትፈርስም፤ አትደረመስም ከሰማይ ልናገር የማልችለው አንድ ጣት ወደ እኔ እየጠቆመች ወፈር ያለ ግርማ ሞገስ ባለው ድምጽ አንድ የማላየው ሰው ለእኔ ተናገረ፤ አንቺን ግን ምሬሻለሁ! አለኝ አለች። ባነንኩ ህልም ነው ብዬ ራሴን ለማሳመንና ነገሩን እምብዛም ክብደት ላለመስጠት በጣሙን ጣርኩ። ይሁንና እየባሰ መጣ እንጂ እንዳሰብኩት ቀለል ማድረግ አልቻልኩም። ሁለት ሦስት ህልም ከዚያ በኋላ አየሁ...ለባሌ ሳማክረው በቤተሰቤ ካገኘሁት እምነት ወጥቼ ወደ እርሱ እንድጠቀለል መከረኝ። ለተግባራዊነቱም ተንቀሳቀስኩ፤ ተምሬ ስጨርስ ልቤ አልሞላ አለኝ! አንድ ትልቅ ክፍተት ይሰማኛል አለች። በህልም ማየት የጀመርኩትም ጉዳይ ቀጥሏል። መዝሙር ለመስማት እሞክራለሁ እጅግ አያለቀስኩ ራሴን አገኛለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ የሚል ጽሁፍ ከመኪና ላይ ተለጥፎ እንኳ አይቼ አለቅሳለሁ። በቃ አብጄ ነው..ያገሩ እብደት ሲጀምር እንዲህ ነው ብዬ ከአንዴም ሁለቴ ደመደምኩ ግን ነገሩ እንደዚያ አይደለም። ያጣሁትና የጎደለኝ አንድ ነገር አለ! እምላክ እያሳየኝ ያለ አንድ የእውነት መንገድ አለ...አንድ እዚህ ምድር የማውቃት ወጣት ጋር ደውዬ እርሷ የምትሄድበት ቤ/ክ እንድትወስደኝ ለመንኳት አለች፤ እርሷም ወደ አንተ መራችኝ፤ እነሆ ዛሬ መጣሁ አለች። ጌታ እራሱ እየመሰከረላት እየሰማሁ የንስሃ ጸሎትን እንኳ ቆሜ መምራት ስላቃተኝ ተንበርክኬ ፡እኔ ከምልሽ ቀጥለሽ በማለት ክርስቶስን የህይወትሽ አዳኝ ና ጌታ አድርገሽ ትቀበያለሽ? አልኳት በደስታ ተቀበለች። ጸሎት ጨርሰን እንኳን ደስ አለሽ ብዬ ፊቷን ስመለከት ፊቷ በማያቋርጥ እንባ ታጥቧል። ጌታ ራሱ የነካት ሴት! ከእርሷ ከተለየሁ በኋላ ለምን ወደ እኛ እንደመጣች ሳጤን ያገኘሁት የሐሥ 12 ጴጥሮስ ሊገደልበት ከነበረው እስር ቤት መልዐክ ተልኮለት በተዓምር ከወጣ በኌላ ወዲያው የሄደው ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበሩበት ቤት ነው። እነርሱ ሰለጴጥሮ መፈታት እየጸለዩ ነበርና ጌታ ጴጥሮስን ወደዚያ ጸሎት ቤት አመጣው። ሰሞኑን ለብዙዎች መፈታት ምክንያት የሆነ ሪቫይቫል እንዲመጣ እየጸለይን ነውና ይህ መሆኑ እምብዛም አያስገርምም። ሌላ ምስክርነት ይቀጥላል.....
የጌታ ጸጋ ይብዛ
የጌታ ጸጋ ይብዛ
< Let us be witnesses for Christ! >
ReplyForward
|
No comments:
Post a Comment