ደብተራን የሚያድን ጌታ!
በቅርቡ ነው ዩትዩብ ከፍቼ አንድ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ማይክራፎን በእጁ ይዞ። ያለ ምስል ከፊት ለፊት ገጽ ላይ አየሁ ፤ ሁለት ጊዜ ገጹን ስጫን ከፈተልኝ ፤ አጠር ካለ ማስታወቂያ በኋላ አንድ ከጥቂት ዓመታት በፊት የማውቀው ሰው ለጉባኤ ምስክርነቱን እየሰጠ ይታያል። ምስክርነቱ እንደዚህ ነው ተቀጥሮ በሚሰራበት NGO ድርጅት ለስራ ወደ አንድ ራቅ ያለ ቦታ ሲጓዙ... በጣም ረጅም ከሆነ ገደል ውስጥ እርሱንም ይሁን ይዟቸው ይጓዝ የነበሩ የውስጥና የውጭ አገር ሰዎችን ጌታ በተዓምር እንዴት እንዳተረፋቸው ተናግሮ ጌታን ከጉባኤው ግልር እያመሰገነ ነበር። ከዚህ ሰው ጋር ከ10 ዓመት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ከሳሪስ ወደ ስታዲየም የሚሄድ ታክሲ ውስጥ በጋቢናው በኩል ተሳፍሬ ስጓዝ ነበር የተዋወቅነው፤ በወቅቱ ሲጃራ ያጨስ ነበር፣ የሲዲ ማጫወቻው ደግሞ መዝሙር ይዘምራል ፤ በእኔና በሹፌሩ በኩል የነበረ ተሳፋሪ በመሃል እንደወረደ እኔ ወደ ሹፌሩ በኩል ወደቀረበው ጠበብ ያለች የመሃል ወንበር ፎቀቅ አልኩ...እናም "ወንድም! መዝሙሩና ሲጃራው እኮ አይሄድም! ከሚል አስተያየት ንግግሬን ጀመርኩ ...እንድ ሁለት እየተባባልን፣ እያወጋን ተጉዘን የምወርድበት ቦታ ከመድረሱ በፊት አድራሻ- ማለቴ ስልክ ተቀያየርን ፤ ስማችንን እርስ በርስ ተዋወቅን..ሄኖክ እባላለሁ አለኝ ..። ሁለት ወር ያህል አልተገናኘንም ምክንያቱ ደግሞ የእርሱ ስልክ አይሰራም ነበር፤ አንድ ቀን ግን ነግሬው በነበረ አድራሻ ፈልጎ በር አንኳኳ ..ተገናኘን.. ጸሎት ቤት አስገብቼ ጥቂት የሆድ የሆዳችንን አወጋን...በአጭሩ ከአጋንንት ጋር ተባብሮ የሚሰራ፣ብዙዎችን በጥንቆላ ያሳተ፤ በድግምት ለሃብታሞች የሚመትት፤ እንደነገረኝ መተት ሰርቶላቸው ውጭ አገር የሄዱ፣ ንግድ የሰመረላቸው፣ የሚዘፍኑ፣ የሚሮጡ..ምን ልበላችሁ ሁሉ ነገር ከተማ ውስጥ ንጹህ አይመስልም! ተነካክቷል። አንዳንዶቹ ከውጭ አገር በሚልኩት ገንዘብ ሁለት ሚኒባስ ገዝቷል። አንዱ እኔ ባለፈው ዕለት የተሳፈርኩበት መሆኑ ነው...የጥንቆላው መንፈስ የተወራረሰው ...ገዳም ውስጥ ነው። አባቱም ድግምት የሚሰሩ ደብተራ እንደሆኑ ነግሮኛል። ሁለት ልጆችና ...ሌላ አንድ ልጅ አለው፤ ለሁሉም ኃላፊነት አለበት። ማለቴ ወጪዎች አሉበት።...ብዙ ከሰማሁት በኋላ ቃል ክርስቶስ ኢየሱስ ከዚህ ሁሉ ነጻ ሊያወጣህ ይችላል! ዛሬ ራስህን ወደህ ትሰጠዋለህ ወይ? አልኩት። እፈራለሁ! ኪዳን ከአጋንንት ጋር ስለገባሁ ይገድለኛል አለኝ፤ ጌታ ኢየሱስ ነው የሚበልጠው አይገድልህም! አልኩት...እሺ ብሎ ጌታን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ ተቀበለ..ንስሐ ገባ። ክፉ መንፈስም ጮሆ ወዲያው ከእርሱ ወጣ ፤የቀረም ነበር ለካ ..ሌላ ጊዜ በህብረት ጸሎት መካከል ራሱን ገልጦ ከእርሱ ጮሆ ወጣ። ብዙ ትግሎች አሳልፎ፣ ደህንነት ትምህርት ጨርሶ፣ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም የውሐ ጥምቀትን ወሰደ። ይኽው ስንት ዓመት ጌታ ተሸክሞት...እኔ ከአገር ብወጣም ጌታ ከእርሱ ጋር ሆኖ ከክፉ ሁሉ እያዳነው መሆኑን ዩትዩብ ያለሁበት ድረስ ምስክረነትን ይዞልኝ መጣ። ለሰዎች ከመሰከርን በኋላ ለመንፈስ ቅዱስ አሳልፎ መስጠት ያለውን የላቀ ትርፍ አይቻለሁ። ሰዎች ምንም ያህል እስራት ውስጥ ቢሆኑ ጌታ ነጻ ሊያወጣቸው ይችላል። ለማንኛውም ሰው ከመሰከራችሁ በኋላ ማድረግ የሚገባችሁን ብቻ እያደረጋችሁ ቀሪውን ለመንፈስ ቅዱስ ተውለት። ውጤቱን ታያላችሁ! ጌታ ይባርካችሁ ይቀጥላል…
<<Let us be witnesses for Christ!>>
benjabef@gmail.com

good
ReplyDelete